BDU IR

ፍላጎት በ “ያልታበሱ እንባዎች” ረጅም ልቦለድ ከLacanian ንድፈ ሀሳብ አንፃር

Show simple item record

dc.contributor.author ወንድሙ, ቸኮለ
dc.date.accessioned 2024-02-01T07:54:52Z
dc.date.available 2024-02-01T07:54:52Z
dc.date.issued 2016-09
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/15589
dc.description.abstract ጥናቱ ዓብይ ዓላማ አድርጎ የተነሳው ያልታበሱ እንባዎች ልቦለድ ውስጥ ያሉ ገፀ ባህሪያት ፍላጎት እንዴት እንደተገለፀ ማሳየት የሚል ነው፡፡ አነሳሽ ምክንያቴ ከላካኒያን ንድፈ ሀሳብ አንፃር ከዚህ ጥናት በፊት ሁለት አጥኝዎች ጥናት ያደረጉ ቢሆንም ፍላጎት፣ ባይተዋርነት፣ ፋሎ-ሴንትሪዝም፣ ጁዊሶንስ እና ሳይኮ-ፓቶሎጂ የሚሉ ፅንሰ ሀሳቦች ላይ ትኩረት ያላደረጉ በመሆኑ ነው፡፡ ጥናቱ ዓይነታዊ የምርምር ዘዴን እና ቴክስት ትንተና ስልትን የተከተለ ነው፡፡ መረጃውን ለመሰብሰብም ቀዳሚና ካልአይ የመረጃ ምንጮች ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ በጥናቱ መሰረት ያልታበሱ እንባዎች በተሰኘው ልቦለድ ውስጥ ያሉ ገፀ-ባህሪያት ፍላጎታቸውን ለማሳካት የሌላውን ፍላጎት ችግር ውስጥ ሲከቱ እና ስለ ሌላ ምን አገባኝ በማለት ኢጎአቸውን ሲገነቡ ተስተውለዋል፡፡ በፍላጎታቸው እጦት ምክንያትም ገፀ-ባህሪያት ለባይተዋርነት ልምድ መፈጠር፣ ለኢጎ መፈጠር፣ ለመገለልና እውነታን ላለመቀበል ሲጥሩ ታይተዋል፡፡ ገፀ- ባህሪያቱ ከተፈጠረባቸው ድብርት ለመውጣትና የፍላጎት እርካታቸውን ለመሙላት የወሲብ ግንኙነት ሲፈጽሙ፣ ጫት በመቃም ከደስታ በላይ የሆነ ደስታ ለማግኘት ጁዊሶንሳቸውን ሲሞሉ ይታያሉ፡፡ ሴት ገፀ- ባህሪያት ባለው አባዊ ስርዓት ምክንያት ውስጣዊ ፍላጎታቸውና ድብቅ ማንነታቸውን ለመግለፅ ሲቸገሩ የታዩ ሲሆን በዚህም የፋሎ ሴንትሪዝም ፅንሰ ሀሳብ በተግባር መከሰቱ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ በመጨረሻም ጥናቱ ያረጋገጠው ገፀ ባህሪያት በፍላጎት እጦት ምክንያት በእንቅልፍ መረበሽ፣ ካለፈ ጊዜ ልምድ ጋር ግጭት መፍጠር፣ በናፍቆት ከውጫዊ እና ውስጣዊ ሀይል ጋር መጋጨት፣ ፍርሐት፣ ጭንቀት፣ ከህይወትና ሞት ጋር መፋጠጥ ብሎም ለሞት ሲዳረጉ የታዬ ሲሆን ይህ ደግሞ የሰው ልጅ ፍላጎት ማለቂያ የሌለው፣ በድርጊት የተሞላና ሂደታዊ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title ፍላጎት በ “ያልታበሱ እንባዎች” ረጅም ልቦለድ ከLacanian ንድፈ ሀሳብ አንፃር en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record