Abstract:
ይህ ጥናት “የአንባቢያን ምላሽ ንባብ በ‘እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ’ አጭር የልቦለድ መድብል” በሚል የተሰራ ነዉ። ጥናቱን
ለማካሄድ ግላዊና አካዳሚያዊ ገጠመኞች አነሳሽ ምክኒያት ሆነዉ የቀረቡ ሲሆን ይህ ጥናት በ2001 ዓ.ም በደራሲ አዳም
ረታ ከታተመዉ “እቴሜቴ የሎሚ ሽታ” አጫጭር የልቦለድ መድብል ዉስጥ በተመረጡት “እቴሜቴ የሎሚ ሽታ እና
በለስ” ሁለት አጫጭር ታሪኮች ላይ የአንባቢያን ምላሽ ንባብን በማድረግ “እቴሜቴ የሎሚ ሽታ እና በለስ” አጫጭር
ታሪኮችን በመመርመር ተንትኗል። በታሪኮቹ ላይ የተደረገዉ ትንተና ያተኮረዉ በታሪኮቹ ጭብጥ ላይ ነዉ። በተመረጡት
ሁለት ታሪኮች ላይ የአንባቢ ተጠኚዎችን ምላሽ መሰብሰብና መተንተን ዋነኛ አላማዉ አድርጎ የተነሳዉ ይህ ጥናት
በኢትዮጲያ ዉስጥ በአንባቢ ምላሽ ንድፈ ሃሳብ የተሰሩ ጥናቶችን ለመዳሰስ ሞክሯል፤ ተዛማጅ ጥናቶች ማግኘት ግን
ከባድ ነበር። ጥናቱ ዓይነታዊ ምርምር ሲሆን የአንባቢ ምላሽ ንድፈ ሃሳብን ተከትሏል። ለጥናቱ ያገለገሉ መረጃዎች
በቃለመጠይቅ ፣ በጽሁፍ መጠይቅ እና በጥልቅ ንባብ ተሰብስበዋል። ለጥናቱ የተመረጡት ሁለቱ ታሪኮች ከተለያየ ቦታና
ሁኔታ ለተመረጡት አስር ተጠኚዎች እንዲያነቡት ተገርጓል። ታሪኮቹን ካነበቡት ተጠኚዎች ምላሻቸዉ የተሰበሰበዉ
ከሁለት ተጠኚዎች በጽሁፍ መጠይቅ ሲሆን ከቀሩት ስምንት ተጠኚዎች ጋር ደግሞ ቃለ መጠይቅ በማድረግ ነዉ።
በአንባቢ ምላሽ ንድፈ ሃሳብ እሳቤ አንድን ፅሁፍ ሙሉ የሚያደርገዉ አንባቢ አንብቦ ሲተረጉመዉ ነዉ። ይህም ሃሳብ
ሲገለጸ የአንድ ድርሰት ደራሲ ለሚፅፈዉ ሃሳብ አላማና ግብ ቢኖረዉም ድርሰቱን በልኩ ተረድቶ ትርጉም የሚሰጠዉ
አንባቢዉ በመሆኑ ነዉ። ይህም ደራሲዉ የጻፈዉ የፈለገዉን አስቦ ይሆናል እዉነት ደግሞ በራስ አንጻር እና ዕይታ
መሰረት የሚመሰረት ነዉ። ምን አልባት ደራሲዉ ፅፎት ነገር ግን ትርጉሙ ባላሰበዉ መልኩ እንደተደራሲዉ የህይወት
ልምድ ሊተረጎም ይችላል በመሆኑም የአንድ ቴክስት ምሉዕነት የሚኖረዉ አንባቢያኑ ጋር ደርሶ በሚሰጠዉ ትርጉም ነዉ።
ይህም በዚህ ጥናት እንድን ታሪክ ለአስር አንባቢያን በማስነበብ ለአንድ ታሪክ የተለያየ ትርጉም ሲመለስ ያሳያል። በዚህም
የሚፈልጉትን አንድን ድርሰት አንብበዉ የተጻፈዉን እና የተነገረዉን ጭብጥ ብቻ መቀበል እና እንዲቀበሉ ማድረግ
እንደማያስፈልግ የሚያሳይ ነዉ። አንባቢያን አንድን ድርሰት እንደ መነሻ ሃሳብ እንጂ ሙሉ ለሙሉ የተላለፈዉን ተቀብሎ
ዝም ማለት የአንባቢ ልክ መሆን እንደማይገባዉ አንባቢ ምላሽ ንድፈ ሃሳብ ይገልጸል ይህም የንድፈ ሃሳቡ እሳቤ በዚህ
ጥናት ተረጋግጧል። ይህም ለአንድ ታሪክ የተለያየ ትርጉምና ምላሽ መሰጠት ምክኒያቱ አንባቢያን አንድን ፅሁፍ
የሚያነቡት ካላቸዉ የህይወትና የእዉቀት ክህሎት አንፃር እያዛመዱ በመሆኑ ነዉ። ይህም በዚህ ጥናት በሰፊዉ ቀርቧል