BDU IR

ደጋግሞ ማንበብ (Rereading) ብልሃትአማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት የሚማሩ ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ እና የማንበብ ተነሳሽነት ለማጎልበት ያለው አስተዋጽኦ፤ በሰባተኛ ክፍል በቤኒሻንጉልኛ ቋንቋ አፍፈት ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author ሙሉቀን ተስፋዬ, ተስፋዬ
dc.date.accessioned 2022-12-02T07:07:31Z
dc.date.available 2022-12-02T07:07:31Z
dc.date.issued 2022-11
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14686
dc.description.abstract የዚህ ጥናት አላማ ደጋግሞ ማንበብ ብልሃት የአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ለማሳደግ ያለውን አስተዋጽኦ መመርመር የሚል ነው፡፡ ጥናቱ ፍትነት መሰል (Quasi experimental) ንድፍን የተከተለ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የጋማሀሩ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2014ዓ.ም በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት የሰባተኛ ክፍል በመማር ላይ ከሚገኙ ሰባት የሰባተኛ ከፍሎች መካከል በተራ እጣ ናሙና ሁለቱ የሰባተኛ ክፍሎች የተመረጡ ሲሆን አንደኛው የፍትነት ቡድን ሁለተኛው ደግሞ የቁጥር ቡድን በማድረግ በጥናቱ እንዲሳተፉ ተደርገዋል፡፡ የፍትነቱ ቡድን ተማሪዎች በደጋግሞ ማንበብ ብልሀት ትምህርቱ የሚሰጣቸው ሲሆን የቁጥጥር ቡድኑ ደግሞ ለክፍል ደረጃው በተዘጋጀው በመምህሩ መምሪያና በተማሪው መፅሀፍ መሰረት ትምህርቱ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በስድስት ሳምንት በአስራሁለት ክፍለ ጊዜ ትምህርቱን እንዲማሩ ተደርጓል፡፡ በጥናቱ መረጃ የተሰበሰበባቸው መሳሪያዎች የቅድመና ድህረ ትምህርት አንብቦ መረዳት ፈተና እና የቅድመና የድህረ ትምህርት የማንበብ ተነሳሽነት መለኪያ የጽሁፍ መጠይቅ ናቸው፡፡ አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት መረጃዎች በነፃ ናሙና ቲ ቴስት ተፈትሸው የተገኘው የድህረ ትምህርት የአንብቦ መረዳት ውጤት t (78) = 6.46 p<.001)ሲሆን በሁለቱ ቡድኖች መካከል የፍትነት ቡድኑ በልጦ ልዩነት አሳይቷል፡፡ ደጋግሞ ማንበብ ብልሃት በተማሪዎች አንብቦ መረዳት ችሎታ ላይ ያሳደረው የተጽእኖ መጠን ኮህንዲ ቀመር ተሰልቶ ውጤቱም 1.45 (በጣም ከፍተኛ) ሆኗል፡፡ በተመሳሳይ የሁለቱ ቡድኖች የድህረ ትምህርትየማንበብ ተነሳሽነት ፁሁፍ መጠይቅ ውጤት በነፃ ናሙና ቲ ቴስት የተተነተነ ሲሆን በተገኘው ውጤት መሰረት ጉልህ ልዩነት መኖሩ ተረጋግጧል ውጤቱም t(48.16) = 14.50 ሲሆን ደጋግሞ ማንበብ ብልሀት በተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያሳደረው ተፅእኖ መጠን በኮህንዲ ቀመር ተሰልቶ d = 3.61 (በጣም ከፍተኛ ሆኗል)፡፡ የጥናቱን ግኝቶች መሰረት በማድረግም ስነ ትምህርታዊ የመፍቴህ ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡ የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችም በጥናቱ ምእራፍ መጨረሻ (ምዕራፍ አምስት) ላይ ተቀምጧል en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title ደጋግሞ ማንበብ (Rereading) ብልሃትአማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት የሚማሩ ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ እና የማንበብ ተነሳሽነት ለማጎልበት ያለው አስተዋጽኦ፤ በሰባተኛ ክፍል በቤኒሻንጉልኛ ቋንቋ አፍፈት ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record