Abstract:
የዚህ ጥናት ዓላማ መናገር ብልሃት የአማርኛ ኢ አፍፈት የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ለማሳደግ የሚኖረውን አስተዋጽኦ መፈተሸ ሲሆን ጥናቱ የተካሄደውም በሁለት ቡድኖች ቅድመትምህርተና ድህረትምህርት ፍትነት መሰል ስልት ነው፡፡በዚህ መሰረትም ጥናቱን ለማከናውን የጊንጭ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በአመቺ ናሙና ተመርጧል፡፡በተመረጠው ት/ቤትከሚገኙት አራት የሰባተኛ ክፍል የመማሪያ ክፍሎች 7A እና 7B ክፍል ተማሪዎች በቀላሉ የእጣ ናሙና ዘዴ ተመርጠዋል፡፡ለጥናቱ የመረጃ መሰብሰቢያ ነት የአንብቦ መረዳት ፈተናና የማንበብ ተነሳሽነት የፅሁፍ መጠይቅ ተግባራዊ ሆነዋል፡፡የመረጃመሰብሰቢያ መሳሪያዎቹ ተገቢነታቸውና አሰተማማኝነታቸውም ተፈሻል፡፡በመቀጠልም በቅድመትምህርት ፈተና ሁለት ክፍሎች በችሎታ ተመጣጣኝ መሆናቸው ከተረጋገጠ በሓላ በእጣ የፍትነትና የቁጥጥር ቡድኖች ተብለው ተመድበዋል ፡፡ከዚያም ለትግበራ በተለዩት ምንባቦችና መልመጃዎች የፍትነት ቡድን ተማሪዎች በመልሶ መናገር ብልሃት የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች በመምህር መምሪያ እና በተማሪ መጽሃፍ በተገለጸው መሰረት ለ12ክፍለ ጊዚያት ማንበብን ተምረዋል፡፡በመጨረሻም ሁለቱንም ቡድኖች የድህረ ትምህርት አንብቦ መረዳት ፈተና በመፈተንና የማንበብ ተነሳሽነት የጽሁፍ መጠይቅ በማስሞላት መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡መረጃዎችም እንደየአገባብነታቸው በተገቢ ገላጭና ድምዳሚያዊ ስታትስቲክስ ተተንትነዋል፡፡ከውጤት ትነተነው መረዳት እንደተቻለው የፍትነት ቡድን ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ፈተና አማካይ ውጤት ከቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ፈተና አማካይ ውጤት ጉልህ የሆነ ልዩነት አሳይቷል፡፡t(134)=8.61. p<0.001)::እንዲሁም የፍትነት ቡድን ተማሪዎች የማንበብ ተነሳሽነት የጽሁፍ መጠይቅ አማካይ ውጤት ከቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች አማካይ ውጤት በጉልህ የበለጠ መሆኑን አመልክቷል t(134)=3.41. p=.001)::ከዚህ በመነሳትም ማብራሪያከቀረበ በኋላ መደምደሚያና አስተያየት ተሰጥቷል፡፡