BDU IR

“ራስን የመጠየቅ ብልሃት የአማርኛ ኢ-አፈፈት ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማጎልበት ያለው ሚና”፤ (በዘጠነኛ ክፍል ተተኳሪነት)

Show simple item record

dc.contributor.author መልክዬ, የማታው
dc.date.accessioned 2022-11-29T13:18:19Z
dc.date.available 2022-11-29T13:18:19Z
dc.date.issued 2022-11
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14607
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዓላማ ራስን የመጠየቅ ብልሃት አንብቦ መረዳትን ለማጎልበት ያለው ሚና መመርመር ነበር፤ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2014 ዓ.ም ሆሞሻ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን የተከታተሉ በበርተኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ 169 የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ 82 የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎች በቀላል ዕጣ ንሞና ተመርጠዋል፡፡ጥናቱ ፍትነት መሰል ሲሆን፣ ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት ባለቁጥጥር ቡድን የተከተለ ነበር፡፡ የፍትነት ቡድን ተሳታፊዎች 41ተማሪዎች ራስን የመጠየቅ የማንበብ ብልሃት፣ የቁጥጥር ቡድኑ ተሳታፊዎች 41ተማሪዎች ደግሞ በተማሪ መጽሀፍና በመምህር መምሪያው ላይ በተመለከተው መሰረት ለአስራ አራት ክፍለጊዜያት አንብቦ መረዳትን እንዲማሩ በማድረግ ፍትነቱ ተተግብሯል። ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት መረጃዎች አንብቦ የመረዳት ፈተና ከሁለቱም ቡድኖች ተሰብስበዋል፡፡ አንብቦ የመረዳት ችሎታ መረጃዎች በነፃ ናሙና ቲ-ቴስት ተፈትሿል፤ የነፃ ናሙና ቲ-ቴስትን መሰረት በማድረግ የድህረትምህርት መረጃዎች ውጤቶች እንዳመለከቱት፣አንብቦ በመረዳት ችሎታ አኳያ የተገኘው ውጤትም t(80) = 4.16, P<0.001 d=0.92 ሆኗል። በውጤቱ መሰረትም፣ በሁለቱ ቡድኖች መካከል የፍትነቱ ቡድን በልጦ ጉልህ የስታትስቲክስ ልዩነት መኖሩን ታውቋል። ከዚያም ራስን የመጠቅ የማንበብ ብልሃት የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማሳደግ ጉልህ አዎንታዊ ጠቀሜታ አለው፤ ከሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡ በዚህ ድምዳሜ መሰረት መምህራን ራስን የመጠየቅ ብልሃት ለአንብቦ መረዳት ችሎታ ያለውን አስተዋጽኦ ተገንዝበው፤ ራስን የመጠየቅ ብልሃት ስልቶችን በቀጥታ ቢያስተምሩ፤ ተማሪዎች በሚያነቡበት ጊዜ ራስን የመጠየቅ ብልሃት ስልቶች ቅድሚያ ትኩረት እንዲኖራቸው ቢደረግ መልካም ነው በማለት የመፍትሔ ሃሳብ ተጠቁሟል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title “ራስን የመጠየቅ ብልሃት የአማርኛ ኢ-አፈፈት ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማጎልበት ያለው ሚና”፤ (በዘጠነኛ ክፍል ተተኳሪነት) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record