BDU IR

የሃሳብ ድር የተማሪዎችን የቃላት ዕውቀት ለማሳደግ ያለው ፋይዳ፤ በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author ፈንታዬ, ንጉሴ
dc.date.accessioned 2022-11-23T12:16:54Z
dc.date.available 2022-11-23T12:16:54Z
dc.date.issued 2015-11
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14543
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ የሃሳብ ድር የተማሪዎችን የቃላት እውቀት ለማሳደግ ያለውን ፋይዳ መመርመር ነበር፤ የጥናቱ ተሳታፊዎች በደቡብ ጎንደር ዞን በስማዳ ወረዳ በሚገኘው በወገዳ ሙሉ ሳይክል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰባተኛ ክፍል ተመዝግበው በመማር ላይ ከሚገኙት ስድስት የሰባተኛ ክፍል መማሪያ ክፍሎች መካከል በቀላል እጣ በተመረጡ ሁለት የመማሪያ ክፍሎች የሚማሩ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ ጥናቱ ፍትነት መሰል ቅድመትምህርት ፈተናና ድህረትምህርት ፈተና የቁጥጥር ቡድን (quasi-experimental pretest-posttest comparison group) ንድፍን የተከተለ ነበር። የፍትነቱ ቡድን ተሳታፊዎች (43 ተማሪዎች) በየሃሳብ ድር ብልሃት ቃላትን የማስተማር ብልሃት፣ የቁጥጥሩ ቡድን ተሳታፊዎች (45 ተማሪዎች) ደግሞ በክፍል ደረጃው የመምህር መምሪያና የተማሪ መጽሃፍ በተመለከቱት የማስተማሪያ ተግባራት መሰረት ቃላትን ለአስር ክፍለጊዚያት ተምረዋል፡፡ የቃላት እውቀትን የሚመለከቱ መረጃዎች በቅድመትምህርትና በድህረትምህርት ፈተና ተሰብስበው በነጻ ናሙና ቲ-ቴስት ተተንትነዋል። በቅድመትምህርት ወቅት የሁለቱም ቡድኖች የጥናቱ ተሳታፊዎች በቃላት ችሎታቸው ተመጣጣኝ እንደነበሩ የነፃ ናሙና ቲ-ቴስት ትንተና ውጤቱ አሳይቷል። ከፍትነቱ በኋላ የፍትነቱ ቡድን ተሳታፊዎች ከቁጥጥሩ ቡድን ተሳታፊዎች በልጠው ጉልህ መሻሻል ማሳየታቸውን የነፃ ናሙና ቲ-ቴስት ትንተና ውጤቱ (t(86) = 2.98, P = .004፣ d = 0.63) መሆኑን አመልክቷል። ከዚህ በመነሳትም የሃሳብ ድር ብልሃት የተማሪዎችን የቃላት እውቀት ለማሳደግ ጉልህ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለው፤ ከማለት ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡ከዚህ ጥናት ውጤት መረዳት እንደተቻለው የፍትነቱ ቡድን ተማሪዎች በሃሳብ ድር ዘዴ ቃላትን መማራቸው የቃላት እወቅተ ፈተና ውጤት በከፍተኛ ደረጃ በልጦ ተገኝቷል፤ በመሆኑም የተማሪዎችን የቃላት እውቀት ለማጎልበት ብልሃቱን በተመለከተ በየድረጃው ለሚያስተምሩ ለቋንቋ መምህራንም ሆነ ለተማሪዎች ስልጠና መስጠትና የቃላት ተግባራትንም ለዚህ ብልሃት በሚያመች መንገድ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ጥናት ውጤት መረዳት እንደተቻለው የፍትነቱ ቡድን ተማሪዎች በሃሳብ ድር ዘዴ ቃላትን መማራቸው የቃላት እወቅተ ፈተና ውጤት በከፍተኛ ደረጃ በልጦ ተገኝቷል፤ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title የሃሳብ ድር የተማሪዎችን የቃላት ዕውቀት ለማሳደግ ያለው ፋይዳ፤ በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record