BDU IR

‹‹ሚታዊ ጉዞና ፍለጋ በሐሽማል ልቦለድ››

Show simple item record

dc.contributor.author እንየው, ወርቁ
dc.date.accessioned 2022-10-06T06:23:52Z
dc.date.available 2022-10-06T06:23:52Z
dc.date.issued 2022-09
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14286
dc.description.abstract ይህ ጥናት ሚታዊ ጉዞና ፍለጋ በሐሽማል ረጅም ልቦለድ በሚል ርዕስ የተደረገ ጥናት ሲሆን ዋና አላማው በተመረጠው ልቦለድ ሚታዊ ጉዞና ፍለጋ እንዴት እንደተገለጸ ተንትኖ ማሳየት ነው፡፡ የጉዞ ምዕራፎች፣ የጉዞ አይነቶች፣ የፍለጋ ምዕራፎች፣ የፍለጋ አይነቶች፣ የሚታዊ ጉዞና ፍለጋ የመጨረሻ አላማ ምንነትን፣ ማሳየት የጥናቱ ዝርዝር አላማዎች ናቸው፡፡ አጥኚው እነዚህን አላማዎች ለማሳካት የተጠቀመው የመተንተኛ ዘዴ ደግሞ መዋቅራዊ የትንተና ስልት ነው፡፡ የመዋቅራዊ የትንተና ስልትን በመጠቀም በልቦለዱ ውስጥ ሚታዊ ጉዞና ፍለጋ እንዴት እንደተገለጹ ለማሳየት በልቦለዱ ውስጥ ትረካዎችን በማውጣት ተንትኗል፡፡ በልቦለዱ መለየት፣ መዝለቅና መመለስ የሚሉ ሚታዊ የጉዞ ምዕራፎች መኖራቸው ተብራርቷል፡፡ እንዲሁም ውስጣዊና ውጫዊ የጉዞ አይነቶች የተገለጹበት መንገድ ተተንትኗል፡፡ እንደ ጉዞ ሁሉ ሚታዊ ፍለጋው መለየት፣ መዝለቅና መመለስ የሚሉ የፍለጋ ምዕራፎችን የተከተለ መሆኑ በትንተና ተብራርቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በልቦለዱ ውስጥ መሪው ገጸባህሪ ጠቢቡ ሖረ መሆናቸውን እና በጠቢቡ ሖረ አማካኝነት የፍለጋ ዓይነቶች የሚጨበጡና የማይጨበጡ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡ የህይወት ውሃ፣ ጸበልና ጥንታዊ የጥበብ መጽሃፍት ተጨባጭ የፍለጋ አይነቶች ሲሆኑ ጥበበኛ ትውልድ፣ ሀገር በቀል ጥበባት የመሳሰሉት ደግሞ በረቂቅነት የሚፈለጉ መሆናቸውን በትንተና ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ እንዲሁም በልቦለዱ የሚታዊ ጉዞና ፍለጋ የመጨረሻ አላማ ሀገር በቀል ጥንታዊ ጥበባትን መፈለግ መሆኑን በተለያዩ መሰረታዊ ማሳያዎች ተተንትኖ ተብራርቷል፡፡ በመጨረሻም ሐሽማል ልቦለድ በውስጡ ከሚታዊ ጭብጦች መካከል ጉዞና ፍለጋን በዋናነት የሚያሳይ ግሩም ሚታዊ ልቦለድ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title ‹‹ሚታዊ ጉዞና ፍለጋ በሐሽማል ልቦለድ›› en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record