BDU IR

ወለፈንዲነት በእናት አለም ጠኑ እና በሀሁ በስድስት ወር

Show simple item record

dc.contributor.author መሰረት, አሰፋ
dc.date.accessioned 2022-08-30T12:42:19Z
dc.date.available 2022-08-30T12:42:19Z
dc.date.issued 2014-07
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14058
dc.description.abstract ወለፈንዲነት የህይወትን ትርጉም አልባነት እና የሰው ልጅ ህይወት ወዳሻት የምትመራው ተስፋ ቢስ ፍጥረት መሆኑን የሚያብራራ ፍልስፍና ነው፡፡የዚህ ጥናት ዓላማም ከህልውናዊነት ጭብጦች ውስጥ አንዱ የሆነውን ወለፈንዲነት በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ሁለት የተውኔት ስራዎች ውስጥ አውጥቶ ማሳየት ነው፡፡ ጥናቱ ዓይነታዊ ጥናት በመሆኑ ቴክስቶችን በተገቢው መልኩ በመፈተሽ የገላጭ ስልት እና የቴክስት ትንተናን በመጠቀም ተከናውኗል፡፡ በአማርኛ ሥነ-ጽሑፍ አጥኚዋ ባደረገችው ምልከታ ወለፈንዲነትን እንደ ዋነኛ መመልከቻ መነፅር ወይም መፈከሪያ ንድፈ ሃሳብ በመጠቀም የተደረገ ጥናት ማግኘት አልቻለችም፡፡ በጥናቱ ከወለፈንዲነት መከሰቻ መንገዶች ውስጥ ተደጋግመው የሚነሱትን የህይወትን ትርጉም መሻት፣ የነፃነት፣ ባይተዋርነት፣ ቀቢፀ ተስፋ፣ አፈንጋጭ ቧልት እና ሳታየር እንዲሁም ቋንቋን ያለመግባባት ምንጭ ማድረግ የሚሉት ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡ በተመረጡት ተውኔቶች ውስጥ ያሉት ገፀ- ባህሪያት ከህይወት ወለፈንዲነት ጋር ተግባብተው ለመኖር የሚያደርጉትን ጥረት እና ማግኘት የቻሉትን ውጤት የሚያሳየንም ነው፡፡በተጨማሪም በሁለቱ ተውኔቶች ውስጥ የተከሰቱ የወለፈንዲት መገለጫዎች እንዲሁም ጥቅም ላይ የዋሉበትን መንገድ አንድነት እና ልዩነትም በሚገባ የተዳሰሰበት ጥናት ነው፡፡ተምሳሌታዊ በሆነ መንገድ ተውኔቶቹ በየዘመናቸው የነበረውን ማህበራዊ እውነታ እና የሰው ልጅ ለዝብርቅርቅ ህይወት እንዲሁም ለምታሳድርበት ተፅእኖ እየሰጠ ስላለው ምላሽ ተንፀባርቆበታል፡፡ በአጠቃላይ የጥናቱ ግኝት የህይወት ወለፈንዲነት በተውኔቶቹ ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች እንደ ተንፀባረቀባቸው ያሳያል፡፡በተጨማሪም ይህንን ወለፈንዲነት በምን መንገድ ተቋቁመው ማለፍ እንደቻሉ ይተነትናል፡፡ ለዚህም የአለበርት ካሙን ንድፈ ሃሳባዊ እሳቤዎች ተጠቅሟል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title ወለፈንዲነት በእናት አለም ጠኑ እና በሀሁ በስድስት ወር en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record