Abstract:
ጥናቱ ዓላማ በዋናነት በማስተማር ልምድና በማስተማር ብቃት መካከል ያለውን ተዛምዶ
የመመርመር ዓላማ ያለው ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2012 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ አስተዳደር
ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አማርኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ 30 መምህራን ናቸው፡፡ የጥናቱ መረጃ
ከሁሉም ተጠኝ መምህራን በምልከታ እና በሰነድ ፍተሻ የተወሰደ ነው፡፡ የጥናቱ ስልት
ተዛምዷዊ ሲሆን በማስተማር ልምድና በማስተማር ብቃት መካከል ያለው የተዛምዶ አይነትና
የተዛምዶ መጠን ተፈትሿል፤ የክሩስካል ዋሊስ፣ የስፒርማን የተዛምዶ መወሰኛ ዘዴ እና የቀላል
ድህረት ትንተና የጥናቱን መረጃዎች ከጥናቱ ጥያቄዎች አንጻር ለመተንተን ተግባር ላይ
ውለዋል፡፡ የመምህራን የማስተማር ብቃት በልምዳቸው አኳያ የጎላ ልዩነት እንደሌለው ጥናቱ
አመላክቷል፡፡ ሆኖም 5-10 አመት ልምድ ያላቸው መምህራን በአንጻራዊነት ከ1-5 እና ከ11
አመት በላይ ልምድ ካላቸው መምህራን የተሻለ ብቃት እንዳላቸው የመረጃ ትንተናው
አሳይቷል፡፡ በሁለቱ ተላውጦዎች ማለትም በማስተማር ልምድና በማስተማር ብቃት መካከል
ያለው ተዛምዶ r=0.83 ዝቅተኛ እንደሆነ የጥናቱ ውጤት አመላክቷል፡፡ የማስተማር ልምድ
የማስተማር ብቃትን 4.7% የሚተነብይ ሆኖ ቢገኝም ትንባያው ግን ደካማ ነው፡፡ በመጨረሻም
የጥናቱ ውጤት በማስተማር ልምድና በማስተማር ብቃት መካከል ዝቅተኛ አዎንታዊ ተዛምዶ
መኖሩን ካመላከቱት ቀደምት የምርምር ድራሳናት ጋር ተደጋገፊ ሲሆን ሁለቱ ተላውጦዎች
ዝቅተኛ አሉታዊ ተዛምዶ አላቸው ከሚሉ ጥናቶች ጋር ተደጋጋፊ ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም
ሌሎች ተዛማጅ ተላውጦዎችን እና የምርምር ስልቶችን ከግምት በማስገባት ተጨማሪ
ምርምሮች ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡