BDU IR

በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪዎች የማንበብ ፍላጎትና የተሳታፊነትና የጥንቁቅነት ሰብእናዎች ተዛምዶ፤ በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author በበትሩ ክፍሌ
dc.date.accessioned 2021-09-21T07:18:04Z
dc.date.available 2021-09-21T07:18:04Z
dc.date.issued 2021-09-21
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/12606
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ በተማሪዎች የማንበብ ፍላጎትና በተሳታፊነትና በጥንቁቅነት ሰብእናዎች መካከል ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ተዛምዷዊ ስልት ተከትሏል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በምእራብ ኦሞ ዞን ባቹማ 2ኛ ደረጃ ትምህርትቤት፣ ጋቺት 2ኛ ደረጃ ትምህርትቤትና ጀሙ ህዳሴ 2ኛ ደረጃ ትምህርትቤት በ2013 ዓ.ም 9ኛ ክፍል ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙ አጠቃላይ 463 ተማሪዎች መካከል በእድል ሰጪ የእጣ ንሞና ዘዴ የተመረጡ 81 ተማሪዎች ናቸው፡፡ የጥናቱን አላማ ከግብ ለማድረስ አስፈላጊ መረጃዎች በጽሁፍ መጠይቅ ተሰብስበዋል፡፡ የጽሁፍ መጠይቁ ለማንበብ ፍላጎት መለኪያ 10 ጥያቄዎች፣ ለተሳታፊነት ሰብእና መለኪያ 10 ጥያቄዎችና ለጥንቁቅነት ሰብእና መለኪያ 10 ጥያቄዎችን ይዟል፡፡ በተዛምዶውም ሁለቱም ነጻ ተላውጦዎች ከጥገኛ ተላውጦው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው፡፡ ይሁንና በጥናቱ ውጤት መሰረት በማንበብ ፍላጎትና በተሳታፊነት ሰብእና መካከል ያለው (r= .05, p= .658)እና በማንበብ ፍላጎትና በጥንቁቅነት ሰብእና መካከል ያለው (r= .13, p= .236) ተዛምዶ ጉልህ አይደለም፡፡ ስለዚህ የተሳታፊነትም ሆነ የጥንቁቅነት ደረጃ መጨመርም ሆነ መቀነስ ከማንበብ ፍላጎት መጨመር ወይም መቀነስ ጋር ያለው ግንኙነት በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ በመሆኑም የተሳፊነትም ሆነ የጥንቁቅነት ሰብእናዎች የተማሪዎችን የማንበብ ፍላጎት ለመተንበይ የላቀ ድርሻ የላቸውም፡፡ ስለዚህ መምህራን የተሳታፊነትና የጥንቁቅነት ሰብእናዎች ከተማሪዎች የማንበብ ፍላጎት ጋር ያላቸው ተዛምዶ ጉልህ አለመሆኑን በመረዳት ለተማሪዎች የማንበብ ፍላጎት መጨመር በዚህ ጥናት ውስጥ ያልተካተቱ ሰብእናዎች ወይም ሌሎች አበረታች ጉዳዮች ጉልህ ድርሻ ሊኖራቸው እንደሚችል ከግምት ማስገባት እንዳለባቸው የጥናቱ ውጤት ይጠቁማል፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject አማርኛ- en_US
dc.title በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪዎች የማንበብ ፍላጎትና የተሳታፊነትና የጥንቁቅነት ሰብእናዎች ተዛምዶ፤ በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record