BDU IR

በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በትብብር የመማር ብልሃት የመፃፍ ችሎታን የማጎልበት ሚና፤ በፋግታ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author በብሪቱ ታደለ
dc.date.accessioned 2021-09-07T07:50:08Z
dc.date.available 2021-09-07T07:50:08Z
dc.date.issued 2021-09-07
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/12568
dc.description.abstract የጥናቱ ዋና ዓላማ አማርኛ ቋንቋን በትብብራዊ መማር ብልሃት ማስተማር የተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታ ለማጎልበት የሚኖረውን ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ባለሁለት ቡድን ቅድመ-ድህረትምህርት ፍትነትመሰል ንድፍን ተከትሎ የተጠና ሲሆን በተንታኝ የአቀራረብ ስልት ተካሂዷል። በፋግታ ለኮማ ወረዳ የሚገኙ የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ችጓሊና ፋግታ) ተማሪዎች የዚህ ጥናት ተሳታፊዎች ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ በአመቺ የንሞና ዘዴ ፋግታ የከፍተኛ ትምህርትና መሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በመምረጥ ጥናቱ ተካሂዷል፡፡ ለጥናቱ ውጤታማነትም በቅድመትምህርት መጻፍ ውጤታቸው ተመጣጣኝ የሆኑት የዘጠነኛ ክፍል ሁለት መማሪያ ክፍሎች (9ኛ G እና 9ኛ K) በዓላማ ተኮር የንሞና ዘዴ ተመርጠዋል፡፡ ለጥናቱ የተመረጡት ሁለት ክፍሎችም በተራ የእጣ ንሞና ዘዴ የሙከራ ቡድን (9ኛ G) እና የቁጥጥር ቡድን (9ኛ K) ሆነው ተለይተው መረጃ ሰጥተዋል፡፡ ለጥናቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ለመሰብሰብም ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የመፃፍ ፈተናዎች አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡ በተገኘው ውጤት መሰረትም በቅድመትምህርት ፈተና የሙከራ ቡድን ተማሪዎች የመጻፍ አማካይ ውጤት 18.93 እንዲሁም የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች 19.21 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በመቀጠል የጥናቱ ተሳታፊዎች የድህረትምህርት የመጻፍ አማካይ ውጤት የሙከራ ቡድን 24.07፣ የቁጥጥር ቡድን 22.77 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይህም አማርኛ ቋንቋን በትብብራዊ መማር ብልሃት ማስተማር የተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታ በአማካይ በ 5.40 እንዲሁም በተለምዷዊው የማስተማር ስልት የጽህፈት ክሂልን ማስተማር በ 3.56 ከፍ እንደሚያደርግ (እንደሚያጎለብት) አመልክቷል፡፡ በድህረትምህርት የመጻፍ አማካይ ውጤት የተመዘገበው የጉልህነት ደረጃም (P<0.001) ከመቁረጫ ነጥቡ (0.05) አንሶ በመገኘቱ በሁለቱም ቡድኖች የተመዘገበው የድህረትምህርት የመጻፍ ውጤት ከቅድመትምህርት የፈተና ውጤት በስታቲስቲክስ ጉልህ ልዩነት እንዳላቸው እንዲሁም በትብብራዊ መማር ብልሃት ማስተማር በመደበኛው የማስተማር ስልት ከማስተማር የበለጠ የተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታ ለማጎልበት እንደሚረዳ አረጋግጧል፡፡ በመጨረሻም አጥኚዋ የጥናቱን ግኝት መሰረት በማድረግ በአማርኛ ቋንቋ መምህራን፣ በተማሪዎች፣ በመርሀ ትምህርት ዝግጅት ባለሙያዎች እና በተመራማሪዎች ሊፈጸሙ የሚገባቸውን የመፍትሄ ሃሳቦች ጠቁማለች፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject አማርኛ- en_US
dc.title በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በትብብር የመማር ብልሃት የመፃፍ ችሎታን የማጎልበት ሚና፤ በፋግታ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record