Abstract:
ይህ ጥናት የተሰራዉ በ በእንባ ሸለቆ ረጅም ልቦለድ ላይ ሲሆን የጥናቱ አላማ የገጸ ባህሪያት
ጭንቀት በእንባ ሸለቆ ረጅም ልቦለድ ዉስጥ ምን እንደሚመስል መፈተሸ ነዉ፡፡የጥናቱ የአጠናን
ዘዴ አይነታዊ ሲሆን የመተንተኛ ስልቱም በአይነታዊ የመተንተኛ ስልት ቴክስት ትንተና
ነዉ፡፡በዚህም የጭንቀት መነሻ ምክንያት፣የሚያስከትላቸዉ ዉጤቶችና የመከላከያ መንገዶች
ከስነልቡና መከላከል ጋር የትንታኔዉ መፈተሻ ንድፈሀሳባዊ መሰረቶች ሆነዋል፡፡በዚህ መንገድ
ሲፈተሽም በእንባ ሸለቆ ልቦለድ ዉስጥ ያሉት ገጸባህሪያት በተለያየ መነሻ ምክንያት ወደ ህይወት
መመሰቃቀል ሲገቡና በዚህ ጭንቀታቸዉ ምክንያት በህይወታቸዉ ላይ የተለያዩ ምልክቶች ወይም
ደግሞ ጭንቀት የሚያስከትላቸዉ ዉጤቶች ተቋዳሽ ሁነዋል፡፡እንዲሁም ደግሞ ጭንቀት ሲበረታ
ለከፍተኛ የአእምሮ ጭንቀት በሽታ እንደሚያጋልጥ ሁሉ እነሱም የተጋለጡ ሁነዉ
ተገኝተዋል፡፡ከዚህም የተነሳ በዋናነት ስኪዞፈርንያ እና የአእምሮ ዝቅጠት አስከትሎባቸዋል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪም ደግሞ ጭንቀትን ለመከላከል በዋናነት መካድ፣መሰወር፣መገራት፣እልክን
መወጣት፣ፅብረቃ፣ማሳበብ እና ግብረ መልስ የተባሉ የተቋቁሞ ስልቶች ጥቅም ላይ መዋላቸዉ
በጥናቱ ለማየት ተችሏል፡፡አመቺ ሁኔታ በማይኖርበት ጊዜ የተቋቁሞ ስልቶች ሊቋረጡ
መቻላቸዉንም ጭምር ለማየት ተችሏል