BDU IR

ፍላጎት በቃል ኪዳን ረጅም ልቦለድ ውስጥ፤ ከላካንያን የፍካሬ-ልቦና ትችት አንጻር

Show simple item record

dc.contributor.author ዘሪሁን አስረስ
dc.date.accessioned 2020-11-24T06:07:08Z
dc.date.available 2020-11-24T06:07:08Z
dc.date.issued 2020-11-11
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/11617
dc.description.abstract የዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ ርእስ ‹‹ፍላጎት በቃል ኪዳን ረጅም ልቦለድ ውስጥ፤ከLacanian የፍካሬልቦና ትችት አንጻር›› የሚል ነው፡፡ የጥናቱ ዐብይ ዓላማ ‹‹በቃል ኪዳን›› ረጅም ልቦለድ ውስጥ የዋና ገጸ-ባህርያትን ፍላጎቶችን እና የፍላጎት ምንጮችን ማሳየት ነው፡፡ የጥናቱ ወሰን ደግሞ ‹‹በቃል-ኪዳን›› ረጅም ልቦለድ እና በLacanian, ‹‹ፍላጎት››፣ ‹‹የባይተዋርነት›› እና ‹‹ፋለስ›› የሚሉትን ጽንሰ-ሐሳቦች በመመርመር ላይ የተገደበ ነው፡፡ ይህ ጥናት የሥነ-ጽሑፋዊ ጥናት (ሂስ) ስለሆነ አይነታዊ የምርምር ዘዴን እና ቴክስታዊ የትንተና ሥልትን የተከተለ ነው፡፡ መረጃ ለመሠብሠብም ቀዳማይ እና ካልዓይ የመረጃ ምንጮች ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ከመረጃ ትንተናው ዋና ዋና ግኝቶች መካከል የመጀመሪያው፣ ገጸ-ባህርያቱ ፍላጎታቸውን በሌላ እና ሌላ ሥልት ለማሟላት ሲጥሩ ታይቷል፡፡ ሁለተኛው፣የልቦለዱ ገጸ-ባህርያት ፍላጎታቸውን ለማሟላት በሚያደርጉት ጥረት የእኔ እንጂ የሌላው የሚለው ግድ ስለማይላቸው የሌላነት ስሜት ተንጸባርቆባቸዋል፡፡ ሦስተኛው፣የሴት ገጸ-ባህርያቶች ፍላጎት በማኅበረ-ባህላዊ ሕግ ተጽእኖ ሥር የወደቀ ነው፡፡ አራተኛው፣ የትንተና ውጤት በእውናዊ ሥርዓት ውስጥ የገጸባህርያቱ ፍላጎት የተደናቀፈበትን ሁኔታ የሚያሣይ ነው፡፡ በመሆኑም ገጸ-ባህርያቱ ኢ-ንቁ ፍላጎት እጦታቸውን በጽሑፍ (ስንኝ በመቋጠር እና ደብዳቤ በመጻፍ)፣ በሕልም፣ በቅዥት፣ በቁጣ እና በስካር ለመግለጽ ሲጥሩ ይታያሉ፡፡ ቋንቋ የፍላጎት ማሟያ እና ለእጦት ምክንያት እንደሚሆን በትንተናው ታይቷል፡፡ በስድብ ቃላት ፋለስን መነጠቅ እንዳለም ትንተናው ያሣያል፡፡ የልቦለዱ ገጸ-ባህርያት የሚያሳዩት ኢ-ንቁ የሆነ የፍቅር፣የገንዘብ፣የሞት እና የበቀል ፍላጎት ለፍርሃት፣ለጭንቀት፣ለስጋት፣ለስቃይ እና ለእጦት እንደዳረጋቸው ትንተናው ያመላክታል፡፡ የተወሰኑት ዋና ዋና ገጸ-ባህርያት ለሚገጥማቸው ከባድ እጦት፣የአእምሮ ሕመም እንዲሁም ሞት ዋናው መንስኤም ሊሳኩ ያልቻሉት ኢ-ንቁ ፍላጎቶች ናቸው፡፡ ይህም የሰው ልጆች ፍላጎት በእጦት እና በስቃይ የተሞላ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject አማርኛ- en_US
dc.title ፍላጎት በቃል ኪዳን ረጅም ልቦለድ ውስጥ፤ ከላካንያን የፍካሬ-ልቦና ትችት አንጻር en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record