BDU IR

የአማራጭ ምዘናዎች የተማሪዎችን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ የማሻሻል ሚና፤ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሑፍ-ዐማርኛ ትምህርትክፍል አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author በኃይላይ, ተስፋይ
dc.date.accessioned 2019-12-06T09:20:50Z
dc.date.available 2019-12-06T09:20:50Z
dc.date.issued 2019-12-06
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/10030
dc.description.abstract አኅጽሮተጥናት የዚህ ጥናት ዓላማ የአማራጭ ምዘናዎችን የተማሪዎችን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ የማሻሻል ሚና መመርመር ነበር፡፡ ዓላማውን ከግብ ለማድረስም በሁለት ቡድኖችና በሁለት የትግበራ ዙሮች የቀረበ የአመጣጣኝ ንድፍ (Counterbalanced design) ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በጥናቱ ትግበራ ሂደት በ2010 ዓ.ም. በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሑፍ-ዐማርኛ ትምህርትክፍል ይማሩ የነበሩ 49 የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ ከተሳታፊዎች የተሰበሰቡት መረጃዎች በሁለት የትግበራ ወቅቶች ከቀረቡት አጠቃላይ ድርሰት የመጻፍ ችሎታ ፈተናዎች፣ ድርሰት የመጻፍ ንዑሳን ችሎታዎች ምዘናዎች፣ ድርሰት የመጻፍ ሂደታዊ ዕድገት መገምገሚያዎች፣ የተማሪዎች ናሙና ድርሰቶችና የፖርቲፎልዮ ማስታወሻዎች ናቸው፡፡ የተገኙት መረጃዎችም የየመተንተኛ ስልቶቻቸው እሙኖች በገላጭ ስታትስቲክስ ከተፈተሹ በኋላ፣ በፍትነትና በቁጥጥር ቡድኖች መካከል ያለውን ልዩነት ለመመርመር፣ የአጠቃላይ ድርሰት የመጻፍ ችሎታ ፈተናዎች አማካይ ውጤቶች በባዕድ ናሙና ቲ-ቴስትና በአበር ልይይት፣ ድርሰት የመጻፍ ንዑሳን ችሎታዎች በባለብዙ ተላውጦ ልይይትና አበር ልይይት፣ ድርሰት መጻፍን በመማር ረገድ ሂደታዊ ዕድገቱን ለመፈተሽ በዳግም ልኬትና ቅይጥ አበር ልይይት ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ እንዲሁም ከተማሪዎች ናሙና ድርሰቶችና የፖርቲፎልዮ ማስታወሻዎች የተገኙት ዓይነታዊ መረጃዎች ከመጠናዊ መረጃዎቹ ጋር እየተቀናጁ ተተንትነዋል፡፡ በተገኙት ውጤቶች መሠረትም፣ በሁለቱም የትግበራ ወቅቶች የአጠቃላይ ድርሰት የመጻፍ ችሎታ፣ የመጻፍ ንዑሳን ችሎታዎችና የመጻፍ ሂደታዊ ዕድገት አማካይ ውጤቶች የፍትነት ቡድን ከቁጥጥር ቡድን አማካይ ውጤቶች ተሽለውና ጉልህ ( p < .05) ልዩነት ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በተጨማሪም የመጠናዊ መረጃዎቹ ውጤቶች የዓይነታዊ መረጃዎች ድጋፍም አግኝተዋል፡፡ በዚህም መሠረት ከመጠናዊና ከዓይነታዊ መረጃዎች የተገኙት ውጤቶች የአማራጭ ምዘናዎች የተማሪዎችን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ የማሻሻል ሚና እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ የጥናቱ አንድምታም ድርሰት መጻፍን በመማር ሂደት የአማራጭ ምዘናዎች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ በመሆኑም፣ ድርሰት የመጻፍ ትምህርት ይዘቶችና ተግባራት ከአማራጭ ምዘናዎች ጋር አዋህዶ ማቅረብ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡ en_US
dc.language.iso en en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title የአማራጭ ምዘናዎች የተማሪዎችን ድርሰት የመጻፍ ችሎታ የማሻሻል ሚና፤ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሑፍ-ዐማርኛ ትምህርትክፍል አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record