| dc.contributor.author | ማቴዎስ, ወንድሙ | |
| dc.date.accessioned | 2019-11-07T04:13:40Z | |
| dc.date.available | 2019-11-07T04:13:40Z | |
| dc.date.issued | 2019-11-07 | |
| dc.identifier.uri | http://hdl.handle.net/123456789/9986 | |
| dc.description.abstract | አህፅሮተ-ጥናት (Abstract) የጥናቱ ዋና አላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በግለጥያቄ ብልሃት የአንብቦ መረዳት ችሎታን ለማጎልበት ያለው አስተዋጽኦ መፈተሸ ነው፡፡ አላማውን ለማሳካትም ፍትነት መሰል (Quesi expreriment) ስልትን ተከትሎ የተሰራና በአይነቱ ደግሞ መጠናዊ የሆነ ጥናት ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በአምቦ ከተማ በከልቻ በሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2011 ዓ.ም በሁለት የመማሪያ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ሲኖሩ እነሱንም በጠቅላላ የጥናቱ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ በጠቅላይ የንሞና (Comprehensive Sampling) ስልት አማካይነት ተመርጠዋል፡፡ በመሆኑም በ9ኛ AናB ክፍል ውስጥ በእያንዳንዳቸው 42 ተማሪዎች በመኖራቸው በድምሩ 84ቱም የጥናቱ ተሳታፊዎች ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በመሆኑም በግለጥያቄ ብልሃት አንብቦ መረዳትን በግልጽ የሚማሩ የሙከራ ቡድንና በተለመደው መንገድ አንብቦ መረዳትን የሚማሩ የቁጥጥር ቡድን በማድረግ የአንብቦ መረዳትን ትምህርት በ6 ሳምንታት ለ24 ሰዓት ማንበብን እንዲማሩ ተደርጓል፡፡ ከተሳታፊዎቹም በቅድምትምህርትና በድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ችሎታን የሚለኩ መረጃዎች በፈተና ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹም በአማካይ ውጤት፣ በመደበኛ ልይይት፣ በባዕድ ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረትም በቅድመትምህርት ፈተናና በድህረትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት መካከል በስታትስቲክስ ጉልህ ልይነት (p<0.05) ታይቷል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተው፣ በግለጥያቄ ብልሃት አንብቦ መረዳትን የተማሩት የሙከራው ቡድን ተማሪዎች ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና አማካይ ውጤት በተለመደው የማንበብ ማስተማሪያ ዘዴ ከተማሩት የቁጥጥሩ ቡድን ተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ፈተና አማካይ ውጤት (t= -12.95, df = 82, p= .000) ጉልህ ልዩነት አሳይቷል፡፡ በአጠቃላይ የጥናቱ ውጤት ያሳየው በግለጥያቄ አንብቦ መረዳትን ማስተማር የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ በማሳደግ ረገድ ከተለመደው የአንብቦ መረዳት ማስተማሪያ ዘዴ በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ነው፡፡ ከጥናቱ ግኝቶች በመነሳትም በአማርኛ ቋንቋ በግለጥያቄ ብልሃት መማር የተማሪዎችን የማንበብ ችሎታን ያዳብራል ወደሚል ድምዳሜ ተደርሷል፡፡ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ለግለጥያቄ ብልሃት ትኩረት ሰጥተው የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለማዳበር ጥረት እንዲያደርጉ በጥናቱ ተመላክቷል፡፡ | en_US |
| dc.language.iso | en | en_US |
| dc.subject | Ethiopian Languages and Literature - Amharic | en_US |
| dc.title | በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ግለጥያቄ ብልሃት የአንብቦ መረዳት ችሎታን ለማጎልበት ያለው አስተዋፅዖ፤ በአምቦ ከተማ በበከልቻ በሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት | en_US |
| dc.type | Thesis | en_US |