| dc.contributor.author | አዲስዓለም, ዘሪሁን | |
| dc.date.accessioned | 2019-11-07T04:09:53Z | |
| dc.date.available | 2019-11-07T04:09:53Z | |
| dc.date.issued | 2019-11-07 | |
| dc.identifier.uri | http://hdl.handle.net/123456789/9985 | |
| dc.description.abstract | አጠቃሎ የጥናቱ ዋና ዓላማ አፋቸውን በኦሮምኛ ቋንቋ የፈቱ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ድርሰት መጻፍ ጊዜ የሚከሰቱ የሰዋስው ግድፈቶችና የግድፈት ምንጮችን መፈተሸ ነው፡፡ በመሆኑም በጥናቱ በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ድርሰት በመጻፍ ጊዜ የሚፈጽሟቸው ዋና ዋና የሰዋስው ግድፈቶች የትኞቹ ናቸው? ለሰዋስው ግድፈት የሚዳርጓቸው ዋና ዋና የተጽዕኖ ምንጮች ምን ምን ናቸው? ከተጽዕኖ ምንጮቹ በንጽጽር ጎልቶ የታየው የቱ ነው? ችግሩን ለመቀነስ የሚቻለው እንዴት ነው? የሚሉ የጥናቱን ጥያቄዎች ለመመለስ ነበር፡፡ ለዚህም በኦሮምያ ክልል በለገጣፎ እና በለገዳዲ ትምህርት ቤቶች 9ኛ ክፍል የሚማሩ ሶስት መቶ ዘጠና አምስት (395) የኦሮምኛ ቋንቋ አፈ-ፈት ተማሪዎች መካከል አንድ መቶ ሰባ ሁለቱ (172) በቀላል እጣ የንሞና ዘዴ ተመርጠዋል፡፡ ለጥናቱ አስፈላጊ መረጃዎችን ለመሰብሰብ አብይ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ የተማሪዎች የድርሰት ፈተና ሲሆን የመምህራን የጽሁፍ መጠይቅ ደግሞ ደጋፊ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ጥናቱ አይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ ንጥል ጥናት በመሆኑ በነዚህ መሳሪያዎች ከተሰበሰቡት መረጃዎች የተገኙትን ውጤቶች በገላጭ መልክ በመተንተን ለጥናቱ መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ተሞክሯል፡፡ ከድርሰት ትንተናው በተገኘው መረጃ መሰረት ሶስት አብይ የሰዋስው ግድፈት አይነቶች ተለይተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከተቆጠሩት 6956 ግድፈቶች መሀል 5905 (84.89%) በቋንቋ አጠቃቀም ግድፈቶች ምድብ፣ 1016 (14.61%) በቋንቋ አወቃቀር ግድፈቶች ምድብ እና 35 (0.5%) መለየት ባልተቻሉ ግድፈቶች ምድብ እንደተፈጸሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከድርሰት ትንተናው ውጤት እና ከመምህራን መጠይቅ ምላሾች መገንዘብ የተቻለውም ተማሪዎቹ ለፈጸሟቸው ሰዋስዋዊ ግድፈቶች ምንጮቹ የአፍ-መፍቻ ቋንቋ ተጽዕኖ (Inter lingual factors)ና ውስጠ ቋንቋ ተጽዕኖዎች (Intra lingual factors)ናቸው፡፡ ከተጽዕኖ ምንጮቹም በአፍ-መፍቻ ቋንቋ ተጽዕኖ እንደተፈጸሙ የታመኑት 1735 (24.94%)፣ በውስጠ ቋንቋ ተጽዕኖ ምክንያት ደግሞ 5221 (75.06%) ግድፈቶች ሊሆኑ ችለዋል፡፡ በውጤቱም ከአፍ-መፍቻ ቋንቋ ተጽዕኖ ይልቅ በውስጠ ቋንቋ ተጽዕኖ ምክንያት የተፈጸሙት ግድፈቶች በቁጥር ልቀው ተገኝተዋል፡፡ የተጠኝ ተማሪዎቹ የሰዋስው ግድፈቶች እንዲቀንሱ ለሰዋስው ሁነቶች ትኩረት ሰጥቶ ማስተማርና ተማሪዎች በታላሚው ቋንቋ ላይ ያላቸውን አሉታዊ አመለካከቶች መቅረፍ ይቻል ዘንድ ጠንክሮ መስራት ያሻል፡፡ | en_US |
| dc.language.iso | en | en_US |
| dc.subject | Ethiopian Languages and Literature - Amharic | en_US |
| dc.title | የኦሮምኛ ቋንቋ አፈ-ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ በሚጽፉት ድርሰት ላይ የሚስተዋሉ አሉታዊ የሰዋስው ተጽዕኖዎች እና የግድፈት ምንጮች ፍተሻ | en_US |
| dc.type | Thesis | en_US |