| dc.contributor.author | ወንዳለ, እርቅይሁን | |
| dc.date.accessioned | 2019-10-17T04:48:18Z | |
| dc.date.available | 2019-10-17T04:48:18Z | |
| dc.date.issued | 2019-10-17 | |
| dc.identifier.uri | http://hdl.handle.net/123456789/9934 | |
| dc.description.abstract | አህጽሮተ-ጥናት የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የማስተሳሰር ብልሀትን በመጠቀም አንብቦ መረዳትን መማርየተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለማጎልበት የሚኖረውን ሚና መፈተሽ ነው፡፡ ዓለማውን ለማሳካትም ፍትነት መሰል(Quasi-experiment) የጥናቱ ንድፍ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች የይስማላ አጠቃላይ ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት በ2011ዓ.ም በዘጠነኛ ክፍል ሲማሩ የነበሩ በ18 የመማሪያ ክፍሎች ከሚገኙ 936 ተማሪዎች መካከል በተራ የእጣ ንሞና ዘዴ በተመረጡ ሁለት መማሪያ ክፍሎች የተገኙ 104 ተማሪዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም በማስተሳሰር ብልሀት አንብቦ መረዳትን የሚማር ቡድንና ያለማስተሳሰር ብልሀት በተለመደው መንገድ አንብቦ መረዳትን የሚማር ቡድን በማድረግ የአንብቦ መረዳት ክሂል ትምህርትን እያንዳንዱ ቡድን በ4 ሳምንታት ለ12 ክፍለ ጊዜያት ተምረዋል፡፡ከተሳታፊዎቹም ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ችሎታ በፈተና ተለክተው መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹም በአማካይ ውጤት፣ መደበኛ ልይይት፣ በባዕድ ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ግኘትእንዳመለከተውም ያለማስተሳሰር ብልሀት በተለመደው መንገድ አንብቦ መረዳትን ከተማሩት ተማሪዎች ይልቅ በማስተሳሰር ብልሀት አንብቦ መረዳትን የተማሩት በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ጉልህ መሻሻል አሳይተዋል፡፡ ከጥናቱ ግኝት በመነሳት በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በማስተሳሰር ብልሀት አንብቦ መረዳትን መማር የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ያዳብራል፡፡ ከግኝቱ በመነሳትም የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የማስተሳሰር ብልሀትን ተጠቅመው ተማሪዎችን ቢያስተምሩ፤የአማርኛ ቋንቋ ሥርዓተ-ትምህርት ባለሙያዎችና የመማሪያ ማስተማሪያ መጽሀፍትአዘጋጆችም የአንብቦ መረዳት ክሂል ማለማመጃ ርዕሰ ጉዳዮችን ሲመርጡና ተግባራትን ሲያዘጋጁ የማስተሳሰር ብልሀትን ለአንብቦ መረዳት ማስተማሪያ ቢጠቀሙበት የተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ሊሻሻል እንደሚችልስነትምህርትዊ የመፍትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፤የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል፡፡ | en_US |
| dc.language.iso | en | en_US |
| dc.subject | Ethiopian Languages and Literature - Amharic | en_US |
| dc.title | የማስተሳሰር ብልሀት (Connection strategy) የአንብቦ መረዳት ችሎታን ለማጎልበት ያለው ሚና፣(በዘጠነኛ ክፍልተተኳሪነት) | en_US |
| dc.type | Thesis | en_US |