| dc.description.abstract |
አህጽሮተ ጥናት
የጥናቱ ዋና አላማ የ 9ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አንብቦ የመረዳት ብልሀት አጠቃቀም ከአንብቦ መረዳት ውጤታቸው ጋር ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነው፡፡የጥናቱ ተተኳሪዎች በዱከም ከተማ አስተዳደር በሚገኝ ኦዳነቤ ትምህርትቤት በ 2011 ዓ.ም የሚማሩ የ 9ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ የዱከም ኦዳነቤ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ብዛት ሴት= 530 ወ=380 በድምሩ 910 ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ካሉት 14 ክፍሎች (ሴክሽኖች) አራቱን ክፍሎች በሎተሪ የናሙና አመራረጥ በመምረጥ ከየክፍሎቹ 20 ተማሪዎችን በብድግ ብድግ ናሙና ለጥናቱ ተተኳሪ የሆኑ 30 ወንድና 50 ሴት በድምሩ 80 ተማሪዎች በእድል ሰጭ የንሞና ዘዴ ተመርጠዋል፡፡ ከእነሱም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በጽሁፍ መጠይቅና በፈተና ተሰብስበዋል፡፡ የጽሁፍ መጠይቁ የተማሪዎቹን አንብቦ የመረዳት ብልሃት አጠቃቀም ለመመርመር በሚያስችል መልኩ ከተከናወነ በኋላ መረጃዉ ተሰብስቧል፡፡ፈተናው ደግሞ አንብቦ የመረዳት ውጤታቸው ምን እንደሚመስል ለመመርመር ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በሁለቱ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች የተገኙት መረጃዎች በመጠናዊና በአይነታዊ ተተንትነዋል፡፡ የተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ብልሃት አጠቃቀምና አንብቦ የመረዳት ውጤት ምን እንደሚመስል ተመርምሮ የተገኘው ውጤት በነጠላ ናሙና ቲ-ቴስት፣ በአንብቦ የመረዳት ብልሃት አጠቃቀምና በአንብቦ መረዳት ውጤት መካከል ተዛምዶ መኖሩን በፒርሰን ተዛምዶ ሥሌት ቀመር፣አንብቦ የመረዳት ብልሃት አንብቦ የመረዳት ውጤትን ለመተንበይ ያስችል እንደሆነ ለመመርመር በቀላል ድህረት ትንተና ስታስቲካዊ ዘዴዎች ተተንትነዉ ተብራርተዋል፡፡ በትንተናው መሰረት በአንብቦ መረዳት ብልሀትና በአንብቦ መረዳት ውጤት መካከል ጉልህ ተዛምዶ (r=.380 ,P̄= .001 ) ታይቷል፡፡ ይህም አንብቦ የመረዳት ብልሀት ሲጨምር በአንብቦ የመረዳት ውጤት ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ እንዳለው አመላክቷል፡፡ በጥናቱ አንብቦ የመረዳት ብልሀት የአንብቦ መረዳት ውጤትን ለመተንበይ ያስችል እንደሆነ ተመርምሮ በአዎንታዊ የሚተነብይ ሆኖ ተገኝቷል (B = .380, t= 5.486, P= .000)፡፡ በመሆኑም የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ብልሀት አጠቃቀም ከአንብቦ መረዳት ውጤት ጋር በማዛመድ መጠቀም ጠቃሚ መሆኑን አጥኝዋ ትጠቁማለች፡፡ |
en_US |