| dc.contributor.author | ጌጤነሽ, ልሳነወርቅ | |
| dc.date.accessioned | 2018-11-14T03:48:59Z | |
| dc.date.available | 2018-11-14T03:48:59Z | |
| dc.date.issued | 2018-11-14 | |
| dc.identifier.uri | http://hdl.handle.net/123456789/9160 | |
| dc.description.abstract | አጠቃሎ ይህ ጥናት ‹‹እርጅና በተመረጡ የስብሃት ገብረእግዚያብሄር አጫጭር ልቦለዶች፤ ማህበረ-ሥነልቡናዊ ንባብ›› በሚል የተደረገ ነው፡፡ ለጥናቱ የተመረጡት አምስት ስድስት ሰባትና ሌሎች እንዲሁም ቦርጨቅ ከተሰኙ የስብሃት ገብረእግዚያብሄር የአጫጭር ልቦለድ መድብሎች አምስት አጫጭር ልቦለዶች ናቸው፡፡ በተመረጡት አምስት አጫጭር ልቦለዶች ውስጥ ያሉት አዛውንት ገጸባህሪያት የእርጅና ማህበረ-ሥነልቡና ምን እንደሚመስል ትንተና ተደርጓል፡፡ ትንተናው በሥነለቡናዊና ማህበራዊ ፅንሰሃሳቦች ላይ ተመርኩዞ በአሃዳዊ ትንተና (Textual analysis) ስልት ተከውኗል፡፡ በትንታኔው ክፍልም የገጸባህሪያቱ እርጅና በማህበራዊ ሚናቸው ላይ ምን ለውጥ እንዳመጣ፣ ማህበራዊው የሚና ለውጥ (ሽግግር) በስነልቦናቸው ያስከተለውን ተጽዕኖ ምን እንደሚመስል፣ የአዛውንቱ የእርጅና ዘመን ሰኬታማ መሆን አለመሆኑንና እርጅናቸው ስኬታማ እንዲሆን ወይም እንዳይሆን ያደረጉ ያለፉ የህይወት ልምዶቻቸው ምን እንደሚመስሉ አሃዶቹን መነሻ በማድረግ ትንተና ተደርጓል፡፡ በተመረጡት አጫጭር ልቦለዶች ውስጥ ያሉት ገጸባህሪያት ጥሩ ፡፡ በዚህም ምክኒያት እርጅናቸው ሰኬታማ አልነበረም፡፡ ለቅን ሰሜቶቻቸው መጥፋትና ለእርጅናቸው ስኬታማ ያለመሆን ባለፈው ህይወታቸው የኖሩበት ማህበራዊ ሁኔታ አስተዋጾ እንደነበረው በማጠቃለያው ተብራርቷል፡፡ | en_US |
| dc.language.iso | en_US | en_US |
| dc.subject | Ethiopian Languages and Literature - Amharic | en_US |
| dc.title | እርጅና በተመረጡ የስብሃት ገብረእዚአብሄር አጫጭር ልቦለዶች ውስጥ፤ ማህበረ-ሰነልቡናዊ ንባብ | en_US |
| dc.type | Thesis | en_US |