| dc.contributor.author | በእናትላይ, አየነው | |
| dc.date.accessioned | 2018-11-14T03:33:21Z | |
| dc.date.available | 2018-11-14T03:33:21Z | |
| dc.date.issued | 2018-11-14 | |
| dc.identifier.uri | http://hdl.handle.net/123456789/9157 | |
| dc.description.abstract | አጠቃሎ ይህ ጥናት "የምትሃታዊ እውነታ መገለጫዎች በተመረጡ የይስማዕከ ወርቁ ረጅም ልቦለዶች፤ ክቡር ድንጋይ እና የኦጋዴን ድመቶች " በሚል ርዕስ በልቦዶቹ ውስጥ የሚገኙ የምትሃታዊ እውነታ ትረካ መገለጫዎችን መለየት እና በልቦለዶቹ ለቀረቡት ጭብጦች ያላቸውን ሚና ማሳየት ላይ ትኩረት በማድረግ የትረካ ስልቱን መገለጫዎች ይተነተናል፡፡ በጥናቱ ሂደትም በልቦለዶቹ የታዩ የምትሃታዊ እውነታ መገለጫዎች የትኞቹ እንደሆኑ፣ የትረካ ስልቶቹ ለልቦለዶቹ ያላቸው ፋይዳ ምን እንደሆነ እና ለጭብጦቹ ማቅረቢያነት ጥቅም ላይ የዋሉ የትረካ ዘዴዎች ትኞቹ እንደሆኑ ለጥናቱ ግብ መምቻ የቀረቡ ጥያቄዎችን በማንሳት ለጥያቄዎቹ መልስ ለመስጠት በልቦለዶቹ ላይ አሀዳዊ ትንተና ተካሂዷል፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ እና የልቦለዶችን የትረካ ስልት ለመተንተን የሚያግዙ የንድፈ ሀሳብ ቅኝት በምዕራፍ ሁለት ቀርቧል፡፡ የምትሃታዊ እውነታ ምንነት እና መገለጫዎችን አስመልክቶ የተሰጡ ብያኔዎች እና ትንታኔዎች ተዳሰዋል፡፡ በእነዚህ የንድፈ ሀሳብ ቅኝቶች በመታገዝም በልቦለዶቹ ውስጥ የተስተዋሉ የምትሃታዊ እውነታ መገለጫዎች እና ለጭብጦቹ ያላቸው ፋይዳ በምዕራፍ ሶስት ትንተና ተደርጎባቸዋል፡፡ በጥናቱ ማጠቃለያም በተመረጡት ልቦለዶች ውስጥ የምትሃታዊ እውነታ መገለጫዎች ታይተዋል፡፡ ስለሆነም ክቡር ድንጋይ እና የኦጋዴን ድመቶች የተሰኙ የይስማዕከ ወርቁ ረጅም ልቦለዶች የምትሃታዊ እውነታ ሥጽሑፋዊ ስራዎች ስለመሆናቸው ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡ | en_US |
| dc.language.iso | en_US | en_US |
| dc.subject | Ethiopian Languages and Literature - Amharic | en_US |
| dc.title | የምትሃታዊ እውነታ (Magical Realism) መገለጫዎች በተመረጡ የይስማዕከ ወርቁ ረጅም ልቦለዶች፤ ክቡር ድንጋይ እና የኦጋዴን ድመቶች | en_US |
| dc.type | Thesis | en_US |