Abstract:
አህጽሮተ ጥናት
የዚህ ጥናት ዋና አላማ የመለማመድ ብልሀት የመጻፍ ችሎታን እና ተነሳሽነት
ለማጎልበት ያለውን ሚናመመርመርነበር፡፡የጥናቱን ተሳታፊዎችለመምረጥም ከእድል
ሰጭ ናሙና(Random sampling) መካከልቀላልእድልሰጪ ናሙና(simple random
sampling) ዘዴን ተጠቅሟል፡፡ተሳታፊዎቹም በሆጤሁለተኛደረጃ ትምህርትቤት በ
2010 ዓ.ምበዘጠነኛ ክፍል ከሚማሩ ተማሪዎች መካከልበተመረጠው የናሙና ዘዴ
የተመረጡ 50ተማሪዎችናቸው፡፡ የአንድ ቡድንቅድመናድህረልምምድፈተናንድፍን
ተግባራዊያደረገ ነው፡፡ ለተማሪዎች ቅድመ ትምህርትፈተናተሰጥቷል፣ለሁለት ወር
ያክል በአጥኚው ከተማሩ በኋላ የድህረ ትምህርትፈተናውከቅድመ ትምህርትፈተናው
በተመሳሳይ መልክተዘጋጅቶ እንዲፈተኑ ተደርጓል፡፡ ከነዚህ ተማሪዎችም በቅድመ
ትምህርትናበድህረ ትምህርትፈተናዎችና ከጽሁፍ መጠይቅመረጃዎችተሰብስበዋል፡፡
መረጃዎቹምመጠናዊየምርምር ዘዴን በመጠቀም በዳግም ልኬታ ናሙና ቲ-ቴስት
ተሰልተው በገላጭና ድምዳሜያዊ ስታትስቲክስ ተተንትነዋል፡፡ በሁለቱ መረጃ
መሰብሰቢያዎችአማካኝነትየተገኙትመረጃዎችበቅድመትምህርትፈተናአማካይውጤት
(53.63) እና በድህረ ትምህርትፈተናአማካይ ውጤት(62.47) መካከልበስታትስቲክስ
ጉልህ ልዩነት(p<0.05) ታይቷል፡፡ይህምየመለማመድ ብልሀት የተማሪዎችን የመጻፍ
ችሎታ እንደሚያጎለብት አመላክቷል፡፡ የቅድመ ትምህርት የጽሁፍ መጠይቅአማካይ
ውጤት(2.14) እናበድህረ ትምህርትየጽሁፍ መጠይቅአማካይውጤት(2.64) መካከል
በስታትስቲክስ ጉልህልዩነት(p<0.05) መኖሩንአሳይቷል፡፡ጥናቱየመለማመድ ብልሀት
የተማሪዎችን የመጻፍተነሳሽነት እንዳሻሻለ አሳይቷል፡፡ በጥናቱ ውጤትመሰረትም
የተማሪዎችንየመጻፍችሎታለማጎልበትናየመጻፍችሎታቸዉንለማሻሻልየአማርኛቋንቋ
መምህራን የመለማመድ ብልሀትን የተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታ የማጎልበት ሚና
እንዳለውናየመለማመድብልሀት አይነቶችንበመለየትተግባራዊእንዲያደርጉ፣መምህራን
የመጻፍ ክሂል ትምህርት ይዘትን ሲያስተምሩ የሚያስተምሩበትን የማስተማሪያ ዘዴ
በመፈተሽ ለወደፊት አእምሯዊ የመለማመድ ብልሃቶችን ተጠቅመው
ቢያስተምሩ፣መምህራንተማሪዎቻቸውንየመጻፍክሂልይዘትንበክፍልውስጥሲያስተምሩ
በተቻለ መጠንደጋግሞ መፃፍን፣የፃፉትን በመከለስ መፃፍን፣ልዩልዩየመፃፍ ሂደቶችን
ተከትሎ ለመፃፍ የሚያግዟቸውን ብልሃቶች በመጠቀም እንዲጽፉ በማበረታታት
ተማሪዎቻቸውን ቢረዷቸው፤የመማሪያ መፅሀፍ አዘጋጆች የመጻፍ ክሂል ትምህርት
አቀራረብንበተመለከተ፣ ተማሪዎችማንኛዉንም ዓይነትጽሑፎችንመጻፍይችሉዘንድ
የተለያዩየመጻፍተግባራትንእንዲያከናዉኑአመቺየማለማመጃአጋጣሚዎችን አካትተዉ
ቢያዘጋጁ፣የሚሉአስተያየቶችተሰጥተዋል፡፡