BDU IR

የአሆላሌ ጨዋታ ቃል ግጥሞች ፋይዳ ትንተና

Show simple item record

dc.contributor.author ደብረ ወርቅ, ሞላ
dc.date.accessioned 2018-11-05T09:43:34Z
dc.date.available 2018-11-05T09:43:34Z
dc.date.issued 2018-11-05
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/9105
dc.description.abstract አጠቃሎ ይህ ጥናት <<የአሆላሌ ጨዋታ ቃል ግጥሞች ፋይዳ ትንተና>> በሚል ርዕስ የተደረገ ጥናት ነው፡፡ ለጥናቱ መነሻ ምክንያቶች የሆኑት ለጥናት በመረጡት አካባቢዎች የሚኖረው ማህበረሰብ በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ ችግሮች እየተጋለጠ የኖረ በመሆኑ፣ ብሶቱን፣ ጭንቀቱን፣ ጥላቻውንና ተቃውሞውን ወዘተ የሚገባቸውን ቃል-ግጥሞች እየፈጠረ ስሜቱን ሲያንፀባርቅ ቆይቷል፡፡ በአካባቢው በዓላት ወቅት በጥምቀት፣ በሰርግ፣ በእንጨት ሰበራ፣ በነዚህ ሁሉ ገጠመኞች ሳቢያ ማህበረሰቡ የፈጠራቸው ቃል- ግጥሞች ተሰብስበው አልተጠኑም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አሁን ባሉት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ቃል-ግጥሞች የሚከወኑባቸው ማህበራዊና ባህላዊ አጋጣሚወችና ሁኔታወች እየተለወጡና እየቀሩ በመሆናቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፉ የነበሩ ቃል-ግጥሞች እየተረሱ፣ እየተለወጡ፣ በሂደትም እየጠፉ የመሄድ አጋጣሚወች ሰፊ እየሆነ መጥቷል፡፡ በነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ ጥናት አስፈላጊ ሆኗል፡፡ ለዚህ ጥናት ለመረጃ መሰብሰቢያ የተመረጡ አካባቢወች በአምባሰል ወረዳ የሚገኙ ቀበሌወች ናቸው፡፡ የጥናቱ ዋና ዓላማ በተመረጡት አካባቢወች የሚገኙትን የአሆላሌ ጨዋታ ቃል-ግጥሞች ፋይዳ መተንተን ሲሆን፣ እነዚህን አላማዎች ለማሳካት መስክ ላይ የተሰበሰቡት 61 ግጥሞች ናቸዉ፡፡ ቃል ግጥሞቹም በሶሰት ዋና ዋና አርዕስቶች የተከፈሉ ሲሆን የሙገሳ፣ የነቀፌታና የፍችር በሚሉ ጭብጣዊ መከፋፈያዎች ከተግባራዊ ፋይዳቸዉ አንፃር ተደራጅተው ቀርበዋል ማለትም በሙገሳ ቃል ግጥሞች ስር አካባቢንና ወጣቶች/ጎልማሶችን የሚያሞግሱ፣ ልጃገረዶች እርስ በርሳቸው የሚሞጋገሱበት፣ ከተለያዩየሰዉነት መልኮች ጋር የተገጠሙ፣ የፍቅር ስሜትን የሚገልፁ፣ የልጃ ገረዶች የጥርስ፣ የከንፈር፣የአይን፣ ተፈጥሮአዊ ዉበት አጉልቶ የተገለፀበት ሲሆን በነቀፌታ ቃል ግጥሞች ስር ደግሞ ወንዶችን ብቻ የሚተቹና ልጅ ገረዶቹ እርስ በርሳቸዉ የሚነቃቀፉበት በሚል የቀረቡ ሲሆን ፍችር ደግሞ ራሱን ችሎ ቀርቧል፡፡ በእያንዳንዱ ምድብ በተደረገው ትንተና መሰረት፣ ጥናቱን ከደረሰባቸው ግኝቶች መካከል የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የሙገሳና የውዳሴ ቃል-ግጥሞች አካባቢወችንና ሰወችን የሚያሞግሱ ናቸው፡፡ የፍችት ግጥሞቹ ሴቶችና ወንዶች የሚተቹ ሲሆን፣ ሴቶችን የሚተቹት ከሴቶች የሙያ ባልትና ከቁጠባ ጋር በተገናኘ ነው፡፡ ወንዶቹን ከግብርና ሥራና ተያያዥ ጉዳዩች ጋር በተገናኘ ነው፡፡ ከጀግንነትና ከኃላፊነት ጋር ተያይዘው የተተነተኑት ቃል-ግጥሞች ሁሉም ወንዶች ብቻ የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ቃል-ግጥሞቹ የአካባቢውን ማህበረሰብ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ባህላዊ ገጠመኞች የሚያሳይ ስለሆነ የሚመለከታቸው የማህበረሰብ አጥኝወች፣ የታሪክና የስነስብ ተመራማሪወች የስነ-ፀሁፍ ባለሙያወች፣ የትምህርት ባለሙያወች፣ የፖለቲካና የአስተዳደር ሰወች ወዘተ ይህንን ጥናት እንደመነሻ በመጠቀም ለማህበረሰቡ ለማስተዳደርም ሆነ ለእድገትና ለልማት ቢገለገሉበት የተሻለ ይሆናል፡፡   en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title የአሆላሌ ጨዋታ ቃል ግጥሞች ፋይዳ ትንተና en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record