Abstract:
አጠቃሎ
“ባይተዋርነት በበውቀቱ ስዩም ግጥሞች” የሚል ርእስ ያለው ይህ ጥናትየበውቀቱ ስዩም መድብሎችን በመፈተሽ ባይተዋርነት የተወከለባቸውን 20 (ሃያ) ግጥሞች በመምረጥ የይዘት ትንተና በማድረግ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ የጥናቱ ዘዴ ገላጭ ሲሆን ስልቱ ደግሞ ጭብጥ ትንተና ነው፡፡በመሆኑም ትንታኔው በዋናነት በባይተዋርነት ትችት አንጻር የተመረኮዘ ሲሆን በተለይም የሴማንን የባይተዋርነት አመዳደብ (ማሀበራዊ ባይተዋርነት፣ ለህግና ደንብ ባይተዋር መሆን፣ ለስልጣን ባይተዋር መሆን፣ ግለፍርቀነትና ወለፈንዲነት) በትችት አንጻርነት (ለመተንተኛነት) ተገልግሏል፡፡ በዚህም መንገድ በግጥሞቹ ውስጥ የተቀረጹ ገጸሰቦች የራስን ነባር ባህል ትቶ አዲስ ባህል በመከተል፣ ለትዳር ክብር ባለመስጠት፣ በፖለቲካ /በጭቆና፣ በሙስና፣ የመናገር ነጻነት በማጣት፣ በፍትሃዊነት ችግር/፣ በማህበረሰቡ በመገፋት፣ በመረሳትና ትኩረት በማጣት፣ በወላዋይነት /የሚፈልጉትን መምረጥ ባለመቻል/ እና ለሃይማኖት አስተምሮ ትኩረት ባለመስጠት በአጠቃላይ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊ እና በኢኮኖሜዊ ጉዳዮች ተጫኝነት ለማህበራዊ ባይተዋርነት፣ ለስልጣን ባይተዋር መሆን፣ ለግለፍርቀነትና ለወለፈንዲነት የተዳረጉ እንደሆኑ በትንትኔ ለማሳየት ተሞክሯል፡፡