BDU IR

“ሥነምህዳራዊ ንባብ በይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” እና “በሕማማትና በገና”

Show simple item record

dc.contributor.author አስማረች, ምስክር
dc.date.accessioned 2018-11-01T09:50:34Z
dc.date.available 2018-11-01T09:50:34Z
dc.date.issued 2018-11-01
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/9074
dc.description.abstract አጠቃሎ ይህ ጥናት ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ (2003) እና ሕማማትና በገና (2004) በተሰኙ የአዳም ረታ አጫጭር ልቦለዶች በተመረጡ ታሪኮች ማለትም ከሕማማትና በገና ’’የሳር ልጆች’’ እና ’’ሕማማትና በገናን’’ ፤ከይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ ’’የቢሾፍቱ ልጆች ጥላሞት’’ እና ’’ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድን’’ ላይየተደረገ ስነ ምህዳራዊ ንባብ ሲሆን የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ቁርኝት መመርመር የዚህ ጥናት አላማ ነው፡፡ ስነጽሁፍ ከስነ ምህዳር ጋር ባለው ዝምድና የሰው ልጅ በተፈጥሮው ከተፈጥሮው ጋር ያለውን ቁርኝት ለማሳየት ማስረጃዎችን (Evidence) ከመፅሀፍቱ ላይ በመሰብሰብ የቴክስት ትንተና ተካሂዷል፡፡ በልቦለዶች ውስጥ የተነሱ የተፈጥሮ ገፅታዎች ውስጥ የተፈጥሮን ዝንቅነት (Pacified)፣ማራኪ(Wonder) ውበትና የተራቆተ ገፅታ በመለየት ከስነምህዳር ፅንሰ ሀሳቦች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማስተዋወቅ ብሎም ለማስተሳሰር የጎላ ሚና እንዳላቸው መገንዘብ ተችሏል፡፡እንዲሁም በስርዓተ ምህዳሮች የሚገኙ የተፈጥሮ አካላት ይዘውት የቆሙትን ፆታዊ ውክልናዎችንምበማመላከትተተንትኗል፡፡ በተጨማሪም በሀገራችን የተፈጥሮ አካላት (በመልክአምድሩና በውስጡ ባሉት ተፈጥሮዎች) ላይ እየደረሰ ያለውን ተፅእኖ በልቦለዶቹ በማሳየት ይህም ተፅዕኖ ለሰው ልጅ ህልውና አስጊ መሆኑን በማመላከት ለተፈጥሮ ጥበቃ መነቃቃት የሚጠይቅ መሆኑተመላክቷል፡፡ በልቦለዶች ውስጥ የሰው ልጅ በምንም ሁኔታ ውስጥ ከተፈጥሮ መነጠል እንደማይችል መመልከትም ተችሏል፡፡ ይህም አንደኛው ተፈጥሮ በተገቢው መኖርለሌላኛው ወሳኝና አስፈላጊ መሆኑ የውዴታ ግዴታ እንደሆነ በግልፅ አመላክቷል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Amharic en_US
dc.title “ሥነምህዳራዊ ንባብ በይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” እና “በሕማማትና በገና” en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record