BDU IR

“የነገረ ህላዌ ጭብጦች በአለማየሁ ገላጋይ ቅበላ፤ የነገረ ህላዌ ንባብ”

Show simple item record

dc.contributor.author መለሰች, ተሻገር
dc.date.accessioned 2018-11-01T09:46:56Z
dc.date.available 2018-11-01T09:46:56Z
dc.date.issued 2018-11-01
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/9073
dc.description.abstract አጠቃሎ ይህ ጥናት “የነገረ ህላዌ ጭብጦች በአለማየሁ ገላጋይ ቅበላ፤ የነገረ ህላዌ ንባብ” በሚል ርዕስ የተጠና ነዉ፡፡ የጥናቱ ዘዴ ገላጭ ሲሆን አቀራረቡ ደግሞ ቴክስት ትንተና ነዉ፡፡ ጥናቱ የነገረ ህላዌ ጭብጦች በተመረጠዉቴክስት እንዴት እንደተከሰቱ ከነገረ ህላዌ ንድፈ ሀሳብ አንጻር ፈትጟል፡፡ በቴክስቱ የተቀረጹ ገጸ ባህሪያት ከንቱ በሆነዉ አለም ህልዉናን ለማቆየት ደፋ ቀና የሚሉ፣የማህበረሰብ እሴትና ስነምግባር ገጸባህሪያቱ ከሚስሉትና ከሚቀርጹት አለም ጋር ባለመጣጣሙ ለባይተዋርነት የተጋለጡ፣ ትክክል የሆኑ ነገሮችን ከማድረግና ትክክለኛዉን ማንነታቸዉን ከመረዳት ይልቅ ትክክል ባልሆኑ ጉዳዮች በመሳተፍ ከማይወጡበት የህይወት ዉጥንቅጥ ዉስጥ የገቡ ብሎም የመምረጥ ነጻነታቸዉን ለመጠቀም በሚያደርጉት የህይወት ጉዞ ለተስፋ መቁረጥና ጭንቀት የተዳረጉ ገጸ ባህሪያት የበቀሉበት መሆኑን አብራርቷል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የሰዉ ልጅ ገዳቢ ክስተት የሆነዉ ሞት ቆመዉ በህይወት በሚኖሩት ገጸ ባህሪያት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ያለዉና ይህ ክስተት የህይወታቸዉ አካል መሆኑን በጸጋ ተቀብለዉ ማዋሃድ ያለባቸዉ እዉነት እንደሆነም አብራርቷል፡፡ ስለሆነም በቅበላ የድርሰት ስራ በርከት ባለ መልኩ የነገረ ህላዌ ጭብጦች ባይተዋርነት፣ ከንቱነት፣ተስፋ መቁረጥ፣ ሞት፣ ጭንቀት፣ ነጻነት ፣ትክክለኛ እና ትክክለኛ አለመሆንየሚሉት በገጸ ባህሪያቱ ህይወት በስፋት የተንጸባረቁ በመሆናቸዉ ታሪኩን የነገረ ህላዌ ታሪክነዉ ብሎ ማጠቃለል ይቻላል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Amharic en_US
dc.title “የነገረ ህላዌ ጭብጦች በአለማየሁ ገላጋይ ቅበላ፤ የነገረ ህላዌ ንባብ” en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record