BDU IR

በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሀት አጠቃቀም (Meta Cognitive Reading strategy use) ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ

Show simple item record

dc.contributor.author በሰዓዳ, የኑስ
dc.date.accessioned 2018-03-30T04:04:16Z
dc.date.available 2018-03-30T04:04:16Z
dc.date.issued 2018-03-30
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/8719
dc.description.abstract አህጽሮተ ጥናት የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በተማሪዎች ልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሀት አጠቃቀምና በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ተዛምዷዊ ስልትን ተከትሏል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በሰሜን ጎንደር ዞን፣ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በደጎማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤትና በደንቀዝ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት በ2010ዓ.ም በ10ኛ ክፍል ተመዝግበው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል በእድል ሰጭ የንሞና ዘዴ የተመረጡ 132 ተማሪዎች ናቸው፡፡ በተሳታፊነት ከተመረጡት ተማሪዎች መካከል 6 ያህሉ በፈተናው ዕለት ባለመገኘታቸው ከቀሪዎቹ 126 የጥናቱ ተሳታፊዎች መረጃ እንዲሰበሰብ ተደርጓል፡፡ የጥናቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በጽሁፍ መጠይቅና በአንብቦ መረዳት ፈተና አስፈላጊ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ በልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሀት አጠቃቀምና በአንብቦ የመረዳት ችሎታ መካከል ጉልህ የሆነ አስተማማኝ ተዛምዶ እንዳለ የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡ በተዛምዶውም ችግርፈቺ የማንበብ ብልሀት ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሀት አጠቃቀም የአንብቦ መረዳት ችሎታን የመተንበይ ድርሻው ከፍተኛ እንደሆነም የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡ ከልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሀት አይነቶች መካከል ችግርፈቺ የማንበብ ብልሀት አንብቦ የመረዳት ችሎታን በመተንበይ በኩል ከፍተኛውን ቦታ የያዘ ሲሆን አጠቃላይ የማንበብ ብልሀት ደግሞ አንብቦ የመረዳት ችሎታ በመተንበይ በኩል ሁለተኛ ቦታ ላይ ተቀምጧል፡፡ ነገርግን አጋዥ የማንበብ ብልሀት አንብቦ የመረዳት ችሎታን የመተንበይ ድርሻ እንደሌለው የጥናቱ ውጤት ያመለክታል፡፡ በመሆኑም መምህራን በክፍል ውስጥ የአንብቦ መረዳት ትምህርትን በሚያስተምሩበት ጊዜ የተማሪዎችን ልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሀት አጠቃቀም ከግምት ውስጥ ሊያስገቡ እንደሚገባ የጥናቱ ውጤት ይጠቁማል፡፡ ii iii ማውጫ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject አማርኛ en_US
dc.title በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሀት አጠቃቀም (Meta Cognitive Reading strategy use) ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record