BDU IR

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ የአማርኛ ቋንቋ ፈተና የጥያቄ አቀራረብ ትንተና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተተኳሪነት (ለትምህርት ማስተርስ ድግሪ በከፊል ማሟያነት የቀረበ)

Show simple item record

dc.contributor.author በጥላሁን, በየነ
dc.date.accessioned 2017-10-31T05:04:47Z
dc.date.available 2017-10-31T05:04:47Z
dc.date.issued 2017-11-01
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/8195
dc.description.abstract አህፅሮተ ጥናት የዚህ ጥናት አጠቃላይ ዓላማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከ2005- 2007 ዓ.ም ተዘጋጅተው ለተማሪዎች የቀረቡትን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ የአማርኛ ቋንቋ ፈተና የጥያቄ አቀራረብን /item format/ መተንተን ነው፡፡ ጥናቱ መሠረት ያደረገው የአጠናን ዘዴ በዋናነት ዓይነታዊ ምርምርን ሲሆን አሃዛዊ መረጃዎችን ለመጠቆም ሲባል መጠናዊ የምርምር ዘዴ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በመረጃ ምንጭነት በከተማ አስተዳዳሩ ትምህርት ቢሮ የተዘጋጁት የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ፈተና የጥያቄ ወረቀቶች አገልግሎት ላይ የዋሉት በወሳኝ ንሞና ዘዴ በዓላማ ተኮር ንሞና በመውሰድ ነው፡፡ መረጃውም የተሰበሰበው በሰነድ ፍተሻ ነው፡፡ ለፈተናው የቀረቡት 180 ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ የመልስ አስመራጭ ጥያቄዎች በመሆናቸው ከምርጫ ፈተና አዘገጃጀት መርሆች አንፃር መዘጋጀታቸው ተገምግሟል፡፡ በዚሁ መሰረት የመሪ ጥያቄ አቀራረብን በተመለከተ አምስት መርሆዎችን፣ የአማራጮች አቀራረብ በተመለከተ ስድስት መርሆዎችን በጠቅላላው አስራአንድ መርሆዎችን በመጠቀም ሁሉም ጥያቄዎች ተፈትሸዋል፡፡ በግምገማውም ግልፅና በቂ መረጃ ያልያዙ፣ አሉታዊ ቃላትን በመጠቀም የቀረቡ፣ ጉልህ ፍንጭ ሲጪ የያዙና በአፃፃፍ ስልት ወጥነት የጎደላቸው ጥያቄዎች መኖራቸው ተስተውሏል። በርካታ የአርትኦት ችግሮችም ታይተዋል። በተጨማሪም ሳቢነትና ተአማኒነት የጎደላቸው አሳሳቾች መኖራቸውና አንድ ትክክለኛ መልስ ብቻ እንዲኖራቸው ሆነው ያልተዘጋጁ ጥያቄዎች መኖራቸው እንደችግር ተስተውሏል፡፡ በግምገማው ወቅትም መርሁን ተከትለው የተዘጋጁ ጥያቄዎች መኖራቸው በአዎንታዊነት የሚጠቀስ ነው፡፡ በአጠቃላይ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ስለተፈታኝ ተማሪዎች ጠቃሚና አስተማማኝ መረጃ ለማግኘት የሚያዘጋጃቸውን ፈተናዎች በየጊዜው እየፈተሸ ጥራት ያላቸውን ጥያቄዎችን ለማቅረብ መጣር ይኖርበታል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject አማርኛ en_US
dc.title የ8ኛ ክፍል ክልላዊ የአማርኛ ቋንቋ ፈተና የጥያቄ አቀራረብ ትንተና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተተኳሪነት (ለትምህርት ማስተርስ ድግሪ በከፊል ማሟያነት የቀረበ) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record