BDU IR

በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መር መጻፍ ብልሃት በተማሪዎች የመጻፍ ችሎታ ላይ ያለው ተፅዕኖ “በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት”

Show simple item record

dc.contributor.author አለምአንች, አቤ
dc.date.accessioned 2024-11-21T10:55:42Z
dc.date.available 2024-11-21T10:55:42Z
dc.date.issued 2024-03
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/16243
dc.description.abstract ይህ ጥናት ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የተነሳው በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መር የመጻፍ ብልሃት በተማሪዎች የመጻፍ ችሎታ ላይ ያለውን ተፅዕኖ መመርመር ነው። ጥናቱ ባለሁለት ቡድን ከፊል ሙከራዊ ሲሆን የተካሄደውም በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በጎንጅ ቆለላ ወረዳ በጎንጅ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም ሲማሩ ከነበሩ የ11ኛ ክፍል 81 ተማሪዎች ላይ ያተኮረ ጥናት ነው። የተሳታፊዎቹ አመራረጥ በአሳማኝ ናሙና አመራረጥ ዘዴ ተመርጠዋል። ትምህርት ቤቱ በአመች ንሞና ተመርጧል።የክፍል ደረጃው በዓላማ ተኮር ሆኖ አንድ መምህር ከምታስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ሁለት መማሪያ ክፍሎች በተራ የእጣ ናሙና አመራረጥ ዘዴ ተመርጠዋል። የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያው ቅድመና ድህረ ትምህርት የመጻፍ ፈተናዎች ሲሆኑ የቅድመ ትምህርት የመጻፍ ፈተና ዓላማው በቡድኖቹ መካከል ያለውን የመጻፍ ችሎታ ተመጣጣኝነት ለማረጋገጥ የተሰጠ ነው።ቡድኖቹ የቅድመ ትምህርት የመጻፍ ፈተናውን ከተፈተኑ በኋላ አንዱን ቡድን የሙከራ፣ አንዱ ቡድን የቁጥጥር ቡድን አድርጎ በመመደብ ወደ ትግበራው ተገብቷል።ትግበራውም የሙከራ ቡድኑን በመር መፃፍ ብልሃት የቁጥጥር ቡድኑን በተለመደው መጻፍ ማስተማሪያ ስልት ለአስር ለአስር ክፍለ ጊዜ ከተለማመዱ በኋላ ቡድኖቹ ድህረ ትምህርት የመጻፍ ፈተና ተፈትነዋል።የዚህ ፈተና ዓላማም በቡድኖቹ መካከል የመጣውን የመጸፍ ችሎታ ልዩነት ለማረጋገጥ የተሰጠ ነው።ቅድመና ድህረ ትምህርት የመፃፍ ፈተናዎች በሦስት አራሚዎች በማሳረም፣የተገኘውን ውጤትም በገላጭ ስታቲስቲክሳዊ እና በነፃ ናሙና ቲ ቴስት በመተንተን በቡድኖች መካከል ያለውን የውጤት ተመጣጣኝነትና ልዩነት በትንተናው ተረጋግጧል። የተገኘው ውጤትም የቅድመ ትምህርት የመጻፍ ፈተና ውጤት የሙከራና የቁጥጥር ቡድኖች መካከል ጉልህ የሆነ ልዩነት የሌለው መሆኑ በትንተናው ተረጋግጧል። ውጤቱም የP ዋጋ 0.715 በመሆኑ ከመቁረጫ ነጥቡ ከ0.05 የበለጠ ሆኗል። የድህረ ትምህርት የመጻፍ ፈተና ውጤት ትንተና በሙከራና በቁጥጥር ቡድኖች መካከል ጉልህ የሆነ ልዩነት ያለው መሆኑ በትንተናው ተረጋግጧል። ውጤቱም የP ዋጋ 0.000 በመሆኑ ከመቁረጫ ነጥቡ ከ0.05 ያነሰ ሆኗል። ይህ ውጤትም መር የመጻፍ ብልሃት የተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታ ለማሻሻል አዎንታዊ አስተዋፅኦ አለው ወደሚል ድምዳሜ በመደረሱ ከዚህ በመነሳተም ትምህርታዊና ምርምራዊ አስተያየቶች ቀርበዋል en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መር መጻፍ ብልሃት በተማሪዎች የመጻፍ ችሎታ ላይ ያለው ተፅዕኖ “በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት” en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record