BDU IR

ስላቅ በተመረጡየጌታቸውታረቀኝ የተውኔት ስራዎች

Show simple item record

dc.contributor.author ረድኤት, አስራደ
dc.date.accessioned 2024-01-23T06:42:03Z
dc.date.available 2024-01-23T06:42:03Z
dc.date.issued 2016-01
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/15583
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዓላማ በተመረጡ የጌታቸው ታረቀኝ የተውኔት ስራዎች ዉስጥ ስላቅ በምን መልኩ እንደተከሰተ ማሳየት ነዉ፡፡ በተውኔት ስራዎች ላይ የጥናት ክፍተት መኖሩ እና ተውኔቶቹን በስላቅ ማንጸሪያ መመልከት አመቺ ሆኖ መገኘቱ እንደመነሻ ሃሳብ በመያዝ ተጠንቷል፡፡ ጥናቱ ዓይነታዊ ጥናት በመሆኑ ቴክስቶችን በተገቢው መልኩ በመፈተሽ የገላጭ ስልት እና የቴክስት ትንተናን በመጠቀም ተከናውኗል፡፡ በጥናቱም የስላቅ የመሳለቂያ ዘዴዎች በርካታ ቢሆኑም በዚህ ጥናት ውስጥ ከስላቅ የመሳለቂያ ዘዴዎች ውስጥ አለመመጣጠን፣ ማጋነን፣ማዛባት እና ምጸት ትንተና ተደርጎባቸዋል፡፡ በተመረጡት ተውኔቶች ውስጥ መስተካከል ያለበት ጉዳይ በስላቅ መንገድ ቀርቦ የታየበት ነው፡፡ በተጨማሪም በተውኔቶቹ ውስጥ ለስላቅ የቀረበው ጉዳይ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ይዘት ያለው መሆኑ በስፋት ተቃኝቶበታል፡፡ በተለይም የትኛው አካል ለስላቅ እንደቀረበ በስፋት ተቃኝቶበታል፡፡ በስላቁ የተገኘውግኝት መንግስት፣ ፖለቲከኞች፣ረጅ ድርጅቶች ፣የውጭ መንግስታት፣ስግብግብ ግለሰቦች፣ ከስርአት የወጡ የሀይማኖት አባቶች ፣አስመሳይ ምእመናን እና ሌሎችም ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ህፀፆች በማንሳት ከችግራቸው እንዲውጡ እና መልካም ስራ እንዲሰሩ ትችት ተሰጥቶበታል፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title ስላቅ በተመረጡየጌታቸውታረቀኝ የተውኔት ስራዎች en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record