dc.contributor.author | አገርነሽ, ስላንተ | |
dc.date.accessioned | 2022-11-29T06:41:41Z | |
dc.date.available | 2022-11-29T06:41:41Z | |
dc.date.issued | 2022-11 | |
dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14572 | |
dc.description.abstract | የዚህ ጥናት ዓላማ እያሰቡ የማጋራት ብልሃት የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ለማሳደግ ያለውን ሚና መመርመር ነበር፤ የጥናቱ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወረዳ 05 በመሰረተ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የሚማሩ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው። ጥናቱ ፍትነት መሰል (Quasi-experimental) ሲሆን፣ ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት ባለቁጥጥር ቡድን የምርምር ንድፍን (Control groups pre-test and post-test design) የተከተለ ነበር፡፡ ትምህርት ቤቱ የተመረጠው በአመቺ ንምና ሲሆን በትምህርት ቤቱ ከሚገኙት ስድስት የ8ኛ ክፍል የመማሪያ ክፍሎች መካከል ደግሞ በቀላል እጣ ንሞና 8ኛ "A" የቁጥጥር ቡድን እና 8ኛ"B" ደግሞ የሙከራ ቡድን ሆነው ተመርጠዋል፡፡ የ8ኛ"A" ክፍል ወንድ 23 ሴት 27 ሲሆኑ የ8ኛ"B" ክፍል ደግሞ ወንድ 24 ሴት ደግሞ 26ናቸው ።የሙከራ ጥናቱም ከትምህርት ቤቱ አቻ እና አጎራባች በሆነው የዕውቀት ምንጭ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ50 ተማሪዎች ተከናውኗል፡፡ የሙከራ ቡድኑ በእያሰቡ የማጋራት ብልሃት እየታገዘ የቁጥጥር ቡድኑ ደግሞ ያለ ብልሃቱ ወይም በመምህሩ መምሪያና በተማሪው መፅሀፍ መሠረት ለአስር ሳምንታት ተምረዋል። የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች የአንብቦ መረዳት ፈተናና የማንበብ ተነሳሽነት የፅሁፍ መጠይቅ ሲሆኑ አስተማማኝና ትክክለኛነታችው በሙከራ ጥናቱ ከተረጋገጠ በኋላ ከሙከራና ከቁጥጥር ቡድኖች መረጃዎቹ ቅድመ ትምህርትና በድኅረ ትምህርት ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች በየአይነታቸው ከተደራጁ በኋላ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ጉልህ ልዩነት መኖሩንና አለመኖሩን ለማወቅ ባዕድናሙና ቲ-ቴስትን በመጠቀም ተተንትነዋል፡፡ ከአንብቦ በመረዳት ችሎታ አኳያ የተገኘው ውጤትም t (98) = -3.841 ፣ P = 0.000 ሆኗል፡፡ በሁለቱ ቡድኖች መካከል የሙከራ ቡድን በልጦ ጉልህ ልዩነት መኖሩን አሳይቷል። በማንበብ ተነሳሽነት ረገድ የተገኘው ውጤትም t (98) = -4.220 ፣ P = 0.000 ሆኗል፡፡ እንዲሁም በሙከራ ቡድንና በቁጥጥሩ ቡድን የጥናቱ ተሳታፊዎች መካከል የሙከራ ቡድኑ በልጦ ጉልህ ልዩነት መኖሩን አሳይቷል፡፡ በመሆኑም እያሰቡ የማጋራት ብልሃት የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ለማሳደግ ጉልህ ሚና አለው፤ ከሚል ድምዳሜ ላይ | en_US |
dc.language.iso | en_US | en_US |
dc.subject | Ethiopian Languages and Literature - Amharic | en_US |
dc.title | «እያሰቡ የማጋራት ብልሃት (Thinking Aloud Strategy) የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ለማሳደግ ያለው ሚና» (በስምንተኛ ክፍል ተተኳሪነት) | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |