BDU IR

መጽሐፍ ቅዱሳዊ በይነአሃዳዊነት በተመረጡ የበዕውቀቱ ሥዩም ግጥሞች ውስጥ

Show simple item record

dc.contributor.author ሁናቸውሁናቸው, ወረታው
dc.date.accessioned 2022-09-22T07:02:24Z
dc.date.available 2022-09-22T07:02:24Z
dc.date.issued 2014-08
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/14263
dc.description.abstract ይህ ጥናት “መጽሐፍ ቅዱሳዊ በይነአሃዳዊነት በተመረጡ የበዕወቀቱ ሥዩም ግጥሞች ውስጥ” በሚል ርዕስ የተካሄደ ነው፡፡ ስለሆነም በሶስቱም የደራሲው የግጥም መድብሎች ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መስተጋብር የፈጠሩ ግጥሞችን ተንትኖ የማሳየት ዓላማ አለው፡፡ መድብሎቹ ስብስብስብ ግጥሞች፣ የማለዳ ድባብ እና አዳምኤል የሚሉት የበዕውቀቱ ስራዎች ሲሆኑ፣ በእነዚህም ውስጥ በጥቅስ፣ ንቡር ጠቀሳ፣ ስላቅ፣ ፓስቲሽ እና ገለጽብረቃ የበይነአሃዳዊነት ቴክኒኮችች አማካኝነት፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የተገናኙ ግጥሞችን ዳስሷል፡፡ ጥናቱ አይነታዊ ዘዴን የተከተለ ሲሆን ለዓላማው ተስማሚ የሆኑ ቴክስቶችን እየወሰደ በፍካሬና በገለጻ መልክ ተንትኗል፡፡ ለትንተና የተመረጡት ግጥሞች በዋናነት በአራት ጭብጣዊ እና በሦስት ስልታዊ ጉዳዮች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በይነሃዳዊነት አሳይተዋል፡፡ ፍቅር፣ ትካዜ፣ ፍለጋ እና ሞት በግጥሞቹና መጽሐፍ ቅዱስ መካከል የታዩ በይነአሃዳዊ ጭብጦች ሲሆኑ፣ ዘይቤአዊ አገለላጾች፣ የአተራረክ ስልቶችና ህይታዊ ተሳትፎዎች ደግሞ ሁለቱን ቴክስቶች ያጣመሩ ስልታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ የትንተና ውጤቱም መጸሐፍ ቅዱስ በግጥሞቹ ጥያቄአ፣ ትካዜአዊ፣ ኪናዊ እና ስላቃዊ በሆነ መንገድ ተደጋግሞ እንደተነሳ አሳይቷል፡፡ ከዚህም በመነሳት በአምስቱም የበይአሃዳዊነት ቴክኒኮች መጽሐፍ ቅዱሳን ያጣቀሱ ግጥሞች፣ የድህረዘመናዊ አላባዎችን በብዛት አሳይተዋል የሚል ማጠቃለያ በመስጠት ጥናቱ ተጠናቋል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title መጽሐፍ ቅዱሳዊ በይነአሃዳዊነት በተመረጡ የበዕውቀቱ ሥዩም ግጥሞች ውስጥ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record