BDU IR

‹‹ምንምነት በተመረጡ የኤፍሬም ስዩም የግጥም ስራዎች ውስጥ››

Show simple item record

dc.contributor.author ሜሮን, ጌታቸው
dc.date.accessioned 2022-05-25T12:23:24Z
dc.date.available 2022-05-25T12:23:24Z
dc.date.issued 2012-08
dc.identifier.uri http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/13698
dc.description.abstract ይህ ጥናት ምንምነት በተመረጡ የኤፍሬም ስዩም የግጥም ስራዎች ውስጥ የሚል ነው ፡፡ ምንምነት ፍልስፍናዊ ሀሳብ ሲሆን የሰው ልጅ ለነገሮች ትርጉም ባጣ እና የሚያምንበት የሚጠብቀው በአጠቃላይ ተስፋ ያደረገው እውነት ሲጣረስ (ሲጠፋ) የሚከሰት ብቻ ሳይሆን ሰው ሆኖ በመፈጠር ብቻ በውስጡ የሚያነሳው ዘላለማዊ ጥያቄ ነው፡፡የዚህ ጥናት አላማምከህልውናዊነት ጭብጦች ውስጥ አንዱ የሆነውን የምንነት ፍልስፍና እና ፅንሰ ሀሳቡን ፍቅር እዚ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር ኑ ግድግዳ እናፍርስ እና ሶሊያና ከሚሉ መድበሎች ውስጥ አስራ አራት ግጥሞችን በመውሰድ ተተንትናል፡፡አይነታዊ ጥናት በመሆኑ ሰነዶችን በተገቢው መልኩ በመፈተሸ በገላጭ ስትል እና በቴክስት ትንተና ጥናቱ ተከናናል፡፡ በግጥሞቹ ውስጥ ፍፁም ነፃነትን ተጠቅሞ የሚወሰን ምርጫ ከትውልድ ተነጥሎ የነገን ግብ የማጣት እውነታ ብሎም ራስን በዘላቂነት የሚገለጹበት ሀቅ ማጣት የሚያስከትለው የምንምነት (ባዶነት) መንፈስ እንዴት ተገለጸ የሚለውን ለመመለስ የተነሳው ጥናቱ መነሻው የምንምነት ጽንሰ ሀሳብን መሰረት ያደረገ ጥናት በአማርኛ ስነ ጽሁፍ ውስጥ አለመከናወኑ እና በግጥም ስራዎቹ ውስጥም በስፋት የሰው ልጅ ለህይወት የሚሰጠው ትርጉም አልባነት መነሳቱ ነው፡፡በጥናቱ ስምምነት ይዘቶች ውስጥ ተደጋግመው የተነሱ የነጻነት ከራሰ መነጠል እና የማንነት ቀውስ ይዘቶች ላይ ትኩረት ተደርጋል ፡፡ በተመረጡ ግጥሞች ውስጥ የምንምነት ጭብጦች እንዴት እነደተገለጹ ከህልውናዊነት ንድፈ ሀሳብ አንጻር ፍተሸ ተደርጓል፡፡በግጥሙ ውስጥ ያሉት ገጸ ባህርያት ፍጹማዊ የሆነውን ነጻነታቸውን ተጠቅመው በወሰኑት ውሳኔ ፀፀትን ራስን መጥላትን እና ተስፋ መቁረጥን የሚያስተናግዱ በውጤቱም ህይወት ምንም ናት በማለት ለባዶነት የተጋለጡ መሆናቸው ተብራርቷል፡፡ በግጥሞቹ ውስጥ የትውልድ ተስፋ ቢስነት እና ነገን አለማሰብ እውነታ የሰው ልጅ ለህይወት እየሰጠው ስላለው ትርጉም አልባነት ተነስቷል፡፡የግጥም ስራዎቹንም የባዶነት (ምንምነት) ይዘት የተነሳባቸው በማለት ልናጠቃልላቸው እንችላለን፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title ‹‹ምንምነት በተመረጡ የኤፍሬም ስዩም የግጥም ስራዎች ውስጥ›› en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record