| dc.contributor.author | በንጉስ መለሰ | |
| dc.date.accessioned | 2021-07-22T08:42:58Z | |
| dc.date.available | 2021-07-22T08:42:58Z | |
| dc.date.issued | 2021-07-21 | |
| dc.identifier.uri | http://ir.bdu.edu.et/handle/123456789/12224 | |
| dc.description.abstract | የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ ለምርምር በተመረጠዉ ልቦለድ ዉስጥ የተገለፁ ዋና ዋና የነገረ ህላዌ ጭብጦችን በመዘርዘር ተንትኖ ማቅረብ ነዉ፡፡ይህን ጉዳይ ለማጥናት ምክንያት የሆነዉ ደግሞ ለምርምር የተመረጠዉ ልቦለድ የነገረ ህላዌ ጭብጦች በስፋት ስለሚንፀባረቁበትና በነገረ ህላዌ ሂስ ለማጥናት አመቺ መሆኑ እንዲሁም ልቦለዱ ከዚህ በፊት ጥናት ያልተደረገበት መሆኑ ነዉ፡፡እነዚህ የህልዉናዊ ጭብጦች ከራሱ ከነገረ ህላዌ ፍልስፍና የሚመነጩ በመሆናቸወ ይህ ፍልስፍና በመተንተኛ ስልትነት ጥቅም ላይ ዉሏል፡፡በዚህ መሰረት ለምርምር በተመረጠዉ ልቦለድ ዉስጥ ባሉ ገፀ ባህርያት ህልዉና ዉስጥ ተመላልሰዉ የተከሰቱ ስድስት ዋና ዋና የህልዉና ጭብጦች ማለትም ምርጫ፣ትርጉምን መፈለግ፣ብቸኝነት፣ተፅዕኖ፣ኢ-ምክንያታዊነትና ባዶነት ተዘርዝረዉ እና በነገረ ህላዌ ፍልስፍና መተርጎሚያነት ተተንትነዉ ቀርበዋል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘ በልቦለዱ የተገለፁ የነገረ ህላዌ ጭብጦች የትኞቹ እንደሆኑ፣እነዚህ ጭብጦች መነሻ ምክንያታቸዉ ምን እንደሆና የቀረቡበትን ስልት እንዲሁም በገፀባህሪያቱ ህልዉና ላይ ያስከተሉትን ተፅዕኖ በመተንተን ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ በዚህ መሰረት በዚህ ልቦለድ የቀረቡ የተወሰኑ ገፀባህርያት በምርጫቸዉ ማንነታቸዉን ገንብተዋል፤ ፍላጎታቸዉን ድንበር ሰርተዉ ለይተዋል፡፡ትርጉም ለማግኘት ይጠይቃሉ፤ልዩ ልዩ ተግባራትን ይተገብራሉ፡፡ ትርጉም ሲያጡ ምርጫቸዉን ሞት ያደርጋሉ፡፡በሚደርስባቸዉ የተለያዩ ተፅዕኖዎች ምክንያት የሚኖሩበትን እዉነተኛ ዓለም ይጠላሉ፡፡በህልም ዓለም መኖርን ይመርጣሉ፡፡የቅርብ የሚሉትን ሰዉ (እናትን፣አባትን፣ሚስትን፣የፍቅር ጓደኛን) በሞት ሲያጡ ወይም በሌላ ምክንያት ሲለያዩ የባዶነት ስሜት ዉስጥ ይገባሉ፡፡በሌላ በኩል በጊዜ ምክንያት በእጃችን ያሉ ነገሮች ዋጋቸዉን ያጣሉ፡፡ወደ ምንምነት ይለወጣሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ በልቦለዱ የተገለፁት በዚህ ጥናት የተለዩ ናቸዉ | en_US |
| dc.language.iso | en_US | en_US |
| dc.subject | አማርኛ | en_US |
| dc.title | የህዉናዊነት ጭብጦች ትንተና በትዝታሽ ለእኔ ትዝታዬ ለአንቺ ረጅም ልቦለድ | en_US |
| dc.type | Thesis | en_US |