BDU IR

በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ግብ መጣል አንብቦ የመረዳት ችሎታን በማጎልበት ረገድ ያለው ሚና፤ በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author ጊዜ, ይበልጣል
dc.date.accessioned 2019-11-14T03:14:46Z
dc.date.available 2019-11-14T03:14:46Z
dc.date.issued 2019-11-14
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/10007
dc.description.abstract አህጽሮተ-ጥናት የዚህ ጥናት ዋና አላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ግብ መጣል የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ በማጎልበት ረገድ ያለውን ሚና መፈተሽ ነው፡፡ አላማውን ከግብ ለማድረስ ፍትነት መሰል (Quasi-experimental) የጥናት ስልት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን በዝዋይ ዱግዳ ወረዳ አራጣ ጩፋ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት በ2011 ዓ.ም በዘጠነኛ ክፍል ሲማሩ ከነበሩ በሶስት የመማሪያ ክፍል ከሚገኙ 145 ተማሪዎች መካከል በቀላል እጣ ንሞና ዘዴ በተመረጡ ሁለት መማሪያ ክፍሎች የተገኙ 90 ተማሪዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ግብ በመጣል ዘዴ በመታገዝ ማንበብን የሚማር ቡድንና ያለግብ መጣል ዘዴ በተለመደው መንገድ ማንበብን የሚማር ቡድን በማድረግ አንብቦ የመረዳት ትምህርትን ለተከታታይ 8 ሳምንታት በሳምንት ለሁለት ክፍለጊዜ ያህል ማንበብን ተምረዋል፡፡ ከጥናቱ ተሳታፊዎችም ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት አንብቦ የመረዳት ችሎታ በፈተና አማካይነት መረጃው ተሰብስቧል፡፡ የተሰበሰበው መረጃም በአማካይ ውጤት፣ በመደበኛ ልይይትና በባዕድ ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልቶ ተተንትኗል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተውም ግብ የመጣል ዘዴን ሳይጠቀሙ በተለመደው መንገድ ማንበብን ከተማሩት የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች ይልቅ ግብ በመጣል ዘዴ በመታገዝ ማንበብን የተማሩት የሙከራ ቡድን ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ጉልህ ልዩነቱ (t(88)=2.641፣ p=.010) በመሆን መሻሻል አሳይቶ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም ከጥናቱ ውጤት በመነሳት በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ግብ የመጣል ዘዴን ተጠቅሞ ማንበብን መማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ያጎለብታል ከሚለው ድምዳሜ ተደርሷል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ መምህራን ማንበብን በሚያስተምሩበት ወቅት ግብ የመጣል ብልሃትን ተጠቅመው ቢያስተመሩ፣ አንዲሁም ለተማሪዎች ስለብልሃቱ ተግባራዊ ግንዛቤ ማስጨበጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ጥናት ያልተዳሰሱ ጉዳዮችና የወደፊት የምርምር አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል፡፡ en_US
dc.language.iso en en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ግብ መጣል አንብቦ የመረዳት ችሎታን በማጎልበት ረገድ ያለው ሚና፤ በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record