BDU IR

በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ድርሰት የመፃፍ ተነሳሽነትና የመፃፍ ችሎታ ተዛምዶ፣ በባህር ዳር ከተማ በሹምአቦ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author የዝባለም, መኰንን
dc.date.accessioned 2019-10-17T04:51:26Z
dc.date.available 2019-10-17T04:51:26Z
dc.date.issued 2019-10-17
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/9936
dc.description.abstract አህፅሮተጥናት የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ተነሳሽነትና ድርሰት የመፃፍ ችሎታ መካከል ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነው፡፡ በመሆኑም ጥናቱ ተዛምዷዊ ስልትን ተከትሏል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በባህርዳር ከተማ ሹምአቦ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርትቤት በ2011ዓ.ም በ9ኛ ክፍል ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገኙ ተማሪዎች ውስጥ በቀላል የዕጣ ናሙና ዘዴ የተመረጡ 101 ተማሪዎች ናቸው፡፡ የጥናቱን ኣላማ ከግብ ለማድረስም የሚያስፈልጉ መረጃዎች በፅሁፍ መጠይቅና በፈተና ተሰብሰበዋል፡፡ መረጃዎቹ በገላጭና ተንባይ ስታትስቲክሶች አማካይነት ተተንትነው ተብራርተዋል፡፡ በመረጃ ትንተናው መሰረት ጥናቱ የተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ተነሳሽነት እንዳላቸው አሳይቷል፡፡ የተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ከአማካይ በላይ ሆኖ ታይቷል፡፡ በተጨማሪም በተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ተነሳሽነትና ድርሰት በመፃፍ ችሎታ መካከል አዎንታዊ ተዛምዶ (r=.503, p<.05) እንዳለ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ ከዚህም ሌላ ተነሳሽነት ድርሰት የመፃፍ ችሎታ የመተንበይ ድርሻው ከፍተኛ መሆኑን (R² = .254፣ F= .33.62 ፣ P<.05) የጥናቱ ውጤት አመልክቷል፡፡ በጥናቱ መሰረት አማርኛ የሚያስተምሩ መምህራን የተማሪዎች ድርሰት የመፃፍ ተነሳሽነት ድርሰት በመፃፍ ችሎታ ላይ የራሱ የሆነ ድርሻ እንዳለው በመገንዘብ ትምህርቱን የተማሪዎችን ስሜት በሚያነሳሳ መልኩ ቢያቀርቡ፣ እንዲሁም የተማሪዎችን ድርሰት የመፃፍ ተነሳሽነት ለማጠናከር የሚረዱ ተግባራትን ቢያከናውኑ፣ የስርዓተትምህርት ቀራጮች መርሀትምህርት ሲነድፉ፣ የትምህርት መሳሪያዎች አዘጋጆች የትምህርት መሳሪያዎችን ሲያዘጋጁ፣ የተማሪዎችን ድርሰት የመፃፍ ተነሳሽነትን ላይ ትኩረት መስጠት ቢችሉ፣ በዘርፉ ጥናት ለማካሄድ የሚሹ ተመራማሪዎች ሰፋ ያለ ሙከራዊ ጥናት ቢያካሂዱ የተማሪዎችን ድርሰት የመፃፍ ችሎታ ለማዳበር የሚያደርገው አስተዋጾ ቀላል አይሆንም፡፡ en_US
dc.language.iso en en_US
dc.subject Ethiopian Languages and Literature - Amharic en_US
dc.title በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ድርሰት የመፃፍ ተነሳሽነትና የመፃፍ ችሎታ ተዛምዶ፣ በባህር ዳር ከተማ በሹምአቦ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record