| dc.contributor.author | ካሳ, አባይ | |
| dc.date.accessioned | 2020-02-04T12:54:11Z | |
| dc.date.available | 2020-02-04T12:54:11Z | |
| dc.date.issued | 2020-02-04 | |
| dc.identifier.uri | http://hdl.handle.net/123456789/10112 | |
| dc.description.abstract | የዚህ ጥናት ዋና አላማ የማንበብ ግለብቃት እምነት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለውን ተዛምዶ መፈተሽ ነው፡፡በዚህ ጥናት የተሳተፉትም በጉጂ ዞን በዋደራ ወረዳ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት በ2011 ዓ.ም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ከነበሩ 342 ተማሪዎች በተራ የናሙና ዕጣ ዘዴ መሰረት የተመረጡ 80 የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ ጥናቱ የተከተለው የአጠናን ዘዴም ተዘምዷዊ ነው፡፡በመሆኑም የተማሪዎችን የማንበብ ግለብቃት ለመለካት በፅሁፍ መጠይቅ፤የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውን ለመፈተሸ ደግሞ በአንብቦ መረዳት ፈተና መረጃ ተሰብስቧል፡፡የተሰበሰበው መረጃም በፒርሰን የተዛምዶ ስሌት ቀመር መሰረት ተተንትኗል፡፡በግኝቱ መሰረትም በሁለቱ ተላውጦዎች (በማንበብ ግለብቃት እምነትና በአንብቦ መረዳት ችሎታ) መካከል አወንታዊ ተዛምዶ ተገኝቷል፡፡የተዛምዶው መጠንም 0.085 ሆኗል፡፡ሆኖም ግን የተዛምዶው መጠን ሲታይ ዝቅተኛ በመሆኑ የጉልህነት መጠኑ በ0.05 የስህተት ይሁንታ መጠን(sig)፣በ80 የነፃነት ደረጃ(df)፣ በባለሁለት ጫፍ ፍተሻ(2-tailed) ተፈትሾ የተዛምዶ መጠኑ ጉልህ ያልሆነ ዝቅተኛ የተዛምዶ መጠን እንዳለ ተመልክቷል፡፡ሌላው የማንበብ ግለብቃት እምነታቸው አማካይ ውጤትም በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ እንዲሁም የአንብቦ መረዳት ችሎታቸው አማካይ ውጤትም በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ በተጨማሪም የማንበብ ግለብቃት እምነት ከተማሪዎች ከተገኘው የአንብቦ መረዳት ውጤት ውስጥ 0.7%(R 2 = 0.007) ያህል ድርሻ ብቻ እንደለው ተመልክቷል፡፡በጥናቱ በተገኘው ውጤት መሰረት የተማሪዎች የማንበብ ግለብቃት እምነት የሚያሳድጉ ስልቶችን በመጠቀም የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታን ማሳደግ ያስፈልጋል የሚል የመፍትሄ ሀሳብ ቀርቧል | en_US |
| dc.language.iso | en_US | en_US |
| dc.subject | አማርኛ | en_US |
| dc.title | የማንበብ ግል ብቃት እምነት ከተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ፦በ10ኛ ክፍል ተተኳሪነት | en_US |
| dc.type | Thesis | en_US |